በሴቶች የዓለም ዋንጫ ላይ ተጨዋቿን ያለፈቃዷ የሳመው የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ስልጣን ለቀቀ
የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቤሊያስ በገዛ ፍቃድ ኃላፊነቱን መልቀቁን አስታውቋል
ፊፋ ተጨዋቿን ያለፈቃዷ ስሟል በተባለው ሩቢያለስን ለ3 ወራት ከማንኛውም የውድድር አይነት አግዶታል
በሴቶች የዓለም ዋንጫ ላይ ተጨዋቿን ያለፈቃዷ የሳመው የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትሉዊስ ሩቤሊያስ በራሱ ፍቃድ ኃላፊነቱን ለቀቀ።
የስፔን እግር ኳስ ፌደሬሽን ኃላፊ ሊዩስ ሩቢያልስ በአለም ዋንጫ ድል በሚከበርበት ወቅት ጀኒ ሄርሞሶ የተባለችውን ተጨዋች አፍ ያለፈቃዷ ስሟል በሚል ውግዘት ሲነሳበት መቆየቱ ይታወሳል።
ሩቢያልስ በአውስትራሊያ ሲድኒ በሴቶች የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር እንግሊዝን 1 ለ 0 ላሸነፉት የስፔን ብሔራዊ ቡድን አባላት ሚዳሊያ በሚሸልምበት ወቅት የተጨዋች ሄርሞሶን ከንፈር በመሳሙ ምክንያት ከፍተኛ ቁጣ አስተናግዷል።
የሩቢያለስ ድርጊት ከውጭ እና ከውስጥ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል፤ የመንግስት ባለስልጣናትም ኃላፊነቱን እንዲለቅ እስከመጠየቅም ደርሷል።
የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቤሊያስ ምንመ ጥፋት አልፈጸምኩም፤ ኃፊነቴንም አልቅም በማለት ሲከራከሩ ቢቆዩም በመጨረሻ በገዛ ፍቃድ ኃላፊነቱን መልቀቁን አስታውቋል።
ስፔን የ2023ቱን የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ካሸነፈች በኋላ በደስታ ስሜት ተጫዋቿን በመሳሙ ፊፋ ለ3 ወራት ከማንኛወም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዳገደውም ይታወሳል።
ሉዊስ ሩቤሊያስ በገዛ ፍቃድ ለስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት የመልቀቂያ ዳብዳቤ ማስገባቱን ነው ቢቢሲ የዘገበው።
የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቤሊያስ ለፒርስ ሞርጋን የቴሌቭዥን ሾው እንደተናገረው፤ “አሁን ባለው ሁኔታ ስራዬን መቀጠል አልችልም” ብሏል።
ሉዊስ ሩቤሊያስ ከስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት በተጨማሪም ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንትነት ኃፊነትም መልቀቁን አስታውቋል።