የምስራቅ ሊቢያ ሀይሎች 16 የቱርክ ወታደሮች መግደላቸውን አስታወቁ
የምስራቅ ሊቢያ ሀይሎች 16 የቱርክ ወታደሮች መግደላቸውን አስታወቁ
በጄነራል ከሊፋ ሀፍታር ለሚመራው ጦር ታማኝ የሆነ በምስራቃዊ ሊቢያ የሚገኝ ኃይል በትናንትናው እለት በሰነዘረው ጥቃት 16 የቱርክ ወታደሮች መግደሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ቱርክ በሰሜን አፍሪካ የዉጊያ ተልእኮ በርካታ ሰማእታትን ማጣቷን አምናለች፡፡
ራሱን የሊቢያ ብሄራዊ ጦር ብሎ የሚመራው የከሊፋ ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት ካሊድ አል ማሀጅብ እንደተናገሩት የቱርክ ወታደሮች የተገደሉት ሚስራታ በምትባል የሊቢያ የወደብ ከተማ ነው፡፡
ቱርክ አለምአቀፍ እውቅና ያለውን የብሄራዊ ስምምነት መንግስት ድጋፍ ከመስጠቷ ባለፈ ወታደሮቿን በመላክ በጄነራል ከሊፋ ሀፍታር የሚመራውን ጦር ለማስወጣት እየሰራች ነው፡፡
እንደ ሮይርስ ዘገባ ከሆነ ቱርክ ከራሷ ወታደሮች በተጨማሪ የሶሪያ ወታደሮችን በመላክ ለጄነራሉ ድጋፍ እያደረገች መሆኑ ተገልጿል፡፡