የደን ሀብት ለአካባቢ ጥበቃ የሚያስገኘው የተለየ ጥቅም ምንድን ነው?
ምድር በውሀ እንዳትጥለቀለቅ ከማድረግ ባለፈ ኦክስጅን በከባቢ አየር ላይ የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል
ደን ለሰው ልጆች እና ለፍጥረታት ሁሉ የብዝሀ ህይወት ሚዛንን ያስጠብቃል
የደን ሀብት ለአካባቢ ጥበቃ የሚያስገኘው የተለየ ጥቅም ምንድን ነው?
የዓለማችን የደን ሀብት በየጊዜው እየተመናመነ በመምጣቱ ምድራችን በታሪክ ከፍተኛውን ሙቀት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች።
የደን ሀብት በተለይም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዞችን በመምጠጥ ምድር ላይ ንጹህ ኦክስጅን እንዲኖር ያደርጋሉ።
ለሰው ልጆችን ኦክስጅንንን በማቅረብ የሚታወቁት ተክሎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰት ሙቀትን በመከላከል የማይተካ ሚናም አላቸው።
እንዲሁም የደን ሀብት ለመዝናኛነት በማገልገል የሰው ልጆች የተለየ የተዝናኖት ስሜት እንዲሰማ በማድረግም ይታወቃሉ።
በጎርፍ እና በሌሎች ምክንያቶችም መሬት እንዳይሸረሸር እና ምድር ወደ ምድረ በዳነት እንዳትቀየር ባማድረግም የላቀ ጥቅም አላቸው የደን ሀብቶች።
የምድራችን ሙቀት መጨመርና በሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶች የሰው ልጆች ህይወት እየተመሰቃቀለ ይገኛል።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪነት በየዓመቱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የዘንድሮው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወይም ኮፕ28 በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት በዱባይ የፊታችን ሕዳር ወር ላይ ይካሄዳል።