የቀድሞው የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሚስታቸው በአንድ ጊዜ ህይወታቸው አለፈ
ኔዘርላድን ለአምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ድራይስ ቫን አጅት እና ሚስታቸው በ93 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል
ባልና ሚስቶቹ በሆስፒታል እጅ ለእጅ እንደተያያዙ ባንድ ጊዜ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል
የቀድሞው የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሚስታቸው በአንድ ጊዜ ህይወታቸው አለፈ፡፡
ድራይስ ቫን አጅት አውሮፓዊቷ ኔዘርላንድን ከፈረንጆቹ 1977 እስከ 1982 ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ኔዘርላንድ ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ አድርገዋል በመባል የሚታወቁት እኝህ ጠቅላይ ሚኒስትር በተወለዱ በ93 ዓመታቸው ህይወታቸው እንዳለፈ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
ለ70 ዓመታት ያህል በትዳር የኖሩት እነዚህ ባልና ሚስቶች በእድሜ ምክንት በተከሰተ የማይድን በሽታ ተጠቅተው ነበር የተባለ ሲሆን በህክምና እርዳታ ከዚህ ዓለም እንዲገላገሉ ተደርገዋልም ተብሏል፡፡
የህክምና ባለሙያዎች በሶስት ልጆቻቸው ፈቃደኝነት ሁለቱን ባልና ሚስቶች እጅ ለእጅ እንደተያያዙ ከስቃይ እንዲያርፉ እና ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
የአውሮፓ ጠንቋዮች እና የ2024 ግምቶቻቸው ምን ምን ናቸው?
በበርካታ የአውሮፓ ሀገራት በማይድን ስቃይ እና ህመም ውስጥ ያሉ ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ አልያም በቤተሰባቸው መልካም ፈቃድ አማካኝነት ህይወታቸው እንዲያልፍ የሚፈቅድ ህግ ያላቸው ሲሆን ኔዘርላንድም ይህን ህግ ካጸደቁ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡
የኔዘርላንድ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቫን አጅት የእስራኤል ደጋፊ የነበሩ ሲሆን በ1999 ወደ ቴልአቪቭ ተጉዘው ከጎበኙ በኋላ ግን በይፋ ድጋፋቸውን ለፍልስጤም አድርገው ቆይተዋል፡፡
ከጉብኝታቸው በተጨማሪም ለፍልስጤማዊያን ነጻነት የሚያግዝ ተቋም የመሰረቱ ሲሆን አውሮፓዊን ፍልስጤምን እንዲደግፉ ጥሪ ሲያደርጉም ነበር፡፡
የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት በእሳቸው የአመራር ጊዜ በሳል ውሳኔዎችን እንዳሳለፉ እና ሀገራቸው በእሳቸው እንደምትኮራ ተናግረዋል፡፡