ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት በመነጠሏ ምክንያት በየዓመቱ 178 ቢሊዮን ዶላር እያጣች ነው ተባለ
የለንደን ከተማ ከንቲባ ሳዲቀወ ካን ከህብረቱ ብንወጣም ያሰብነውን ጥቅም እያገኘን አይደለም ብለዋል
ብሪታንያ ከሰባት ዓመት በፊት ነበር በህዝበ ውሳኔ ከአውሮፓ ህብረት አባባነት ራሷን ያገለለችው
ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት በመነጠሏ ምክንያት በየዓመቱ 178 ቢሊዮን ዶላር እያጣች ነው ተባለ፡፡
በፈረንጆቹ 2016 ላይ ብሪታንያ ከመሰረተችው የአውሮፓ ህብረት በህዝበ ውሳኔ የወጣች ሲሆን ሀገሪቱ ከአባልነት የወጣችው ህብረቱ ጥቅሜን እያስከበረልኝ አይደለም በሚል ነበር፡፡
የህዝብ ውሳኔውን ውጤት ተከትሎ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ጄምስ ካሜሩን ከስልጣን የለቀቁ ሲሆን አሁን ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡
የለንደን ከንቲባ ሳዲቅ ካን እንዳሉት ከአውሮፓ ህብረት መውጣታችን ያሰብነውን ጥቅም እያስገኘልን አይደለም ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ብሪታንያ ከህብረቱ በመውጣቷ ምክንያት 178 ቢሊዮን ዶላር በየዓመቱ እያጣች እንደሆነም ከንቲባው ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከንቲባው ያሉበት የብሪታንያ ሰራተኞች ፓርተ ብሪታንያ ከህብረቱ እንዳትወጣ ቢጥርም እንዳልተሳካለት አስታውቋል፡፡
ብሪታንያ ዜጎቿ የውጭ ሀገር ዜጎችን እንዳያገቡ የሚገድብ ህግ አወጣች
ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷ የታሰበውን የኢኮኖሚ ጥቅም ከማስገኘት ይልቅ ዜጎች በኑሮ ውድነት እንዲጎዱ አድርጓልም ብለዋል ከንቲባ ካን፡፡
እንደ ብሪታንያ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ኢንስቲትዩት ጥናት ከሆነ ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት በመነጠሏ ምክንያት ጉዳት በማድረስ ላይ ሲሆን ይህ ጉዳት በቀጣዮቹ ዓመታት እስከ 6 በመቶ እየጨመረ እንደሚሄድ አስታውቋል፡፡
የእንግሊዝ ባንክ ፖሊሲ አውጪ የሖኑት ጆናታን ሀስኬል በበኩላቸው ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት በመውጣቷ ምክንያት በእያንዳንዱ አባወራ/እማወራ በየ ዓመቱ 1 ሺህ ፓውንድ እንዲያጡ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም በ2035 ስራቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥርን ሶት ሚሊዮን እንደሚያደርሰውም ካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ አስታውቋል፡፡