የእስራኤል የቀድሞ ቤኒያሚን ኔታንያሁ አዲስ መንግስት ለመመስረት ኃላፊነት ተቀበሉ
ኔታንያሁ አዲስ የእስራኤል መንግስት የመመስረት ስልጣን ከፕሬዝዳንት አይዚክ ሄርዞግ ተቀብለዋል
ኔታንያሁ ከፈረንጆቹ ከ1996 እስከ 1999 እንዲሁም ከ2009 እስከ 2021 እስራኤልን መርተዋል
የእስራኤል የቀድሞ ቤኒያሚን ኔታንያሁ አዲስ መንግስት ለመመስረት ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ተገለጸ።
የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የቀኝ ዘመም ፓርቲ ከቀናት በፊት በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ 120 መቀመጫ ባለው ፓርላማ አብላጫ ድምጽ አግኝቷል።
ቤንያሚን ኔታንያሁ እሁድ እለት አዲስ የእስራኤል መንግስት የመመስረት ስልጣን ከፕሬዝዳንት አይዚክ ሄርዞግ ተቀብለዋል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ለአንጋፋው መሪ እና የቀኝ አክራሪ አጋሮቻቸው በ120 መቀመጫ ፓርላማ ውስጥ አብላጫ መቀመጫ አግኝተዋል።
64 የሕግ አውጭዎች ፕሬዝዳንት አይዚክ ሄርዞግ ኔታንያሁ መንግሥት እንዲመሰርቱ ኃላፊነቱን እንዲሰጧቸው ባለፈው ሳምንት መክረዋል ተነግሯል።
እስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አዲስ መንግስት እንዲመሰርቱ ኃላፊነት የሰጡት አንጋፋው ፖለቲከኛ እና የቀኝ አክራሪ ፓርቲዎች ጥምረት በፓርላማ ምርጫ በማሸነፉ ነው።
ሄርዞግ በሙስና ክስ ምክንያት በኔታንያሁ እየተካሄደ ያለውን የወንጀል ክስ “አይመለከትም” ግን “በቀላሉ መታየት የለበትም” ብለዋል።
ሆኖም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኔታንያሁ መንግስት ለመመስረት ብቁ ናቸው ሲል ብይን ሰጥቷል።
ናታኒያሁ ካቢኔ ለመመስረት 28 ቀናት ያላቸው ሲሆን፤ ካስፈለገም የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ይኖራቸዋል ተብሏል።
ኔታንያሁ እስራኤልን ከፈረንጆቹ ከ1996 እስከ 1999 ፤ ከዚያም ከ2009 እስከ 2021 ረጅም የስልጣን ዘመን እስራኤልን መርተዋል።