በእስራኤል በተካሄደ ምርጫ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ፓርቲ በአብላጫ ድምጽ እየመራ ነው
እስራኤል በአራት ዓመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ አካሂዳለች
የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዳግም ወደ ስልጣን እንደሚመጡ ይጠበቃል
በእስራኤል በተካሄደ ምርጫ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ፓርቲ አብላጫ ድምጽ እየመራ ነው
በእስራኤል የፖለቲካ አለመረጋጋት ከተከሰት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ አምስተኛዋን ምርጫ ትናንት አካሂዳለች።
የምርጫው ውጤት ዛሬ ይፋ የተደረገ ሲሆን የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ፓርቲ እና አጋር ፓርቲዎች በአብላጫ ድምጽ እየመሩ ነው ተብሏል።
የቤንያሚን ኔታንያሁ ፓርቲ የሆነው ሊኩድ ፓርቲ እና አጋር ፓርቲዎች 120 የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት መቀመጫዎችን እንዳገኙ ሮይተርስ ዘግቧል።
ቤንያሚን ኔታንያሁ የምርጫ ውጤቱ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት "የእስራኤላዊያንን እምነት ማግኘት ችለናል፣ የተረጋጋ መንግስትም እንመሰርታለን" ብለዋል።
እስራኤልን በጊዜያዊነት እየመሩ ያሉት የሪ ላፒድ ፓርቲ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ፓርቲ አብላጫ እንደተወሰደባቸው ተገልጿል።
የምርጫው የመጨረሻ ውጤት ከቀናት በኋላ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ቤንያሚን ኔታንያሁ ዳግም ወደ ስልጣን እንደሚመጡ ይጠበቃል።
በዚህ ምርጫ አብላጫ የምክር ቤት ወንበር ያገኙት ሊኩድ ፓርቲ እና ቀኝ አክራሪ የእስራኤል ፓርቲዎች በጋራ አዲስ መንግሥት እንደሚመሰርቱ ይጠበቃልም ተብሏል።
የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ዳግም ወደ ስልጣን ከተመለሱ በሀገሪቱ አቅቢ ህግ ለተመሰረተባቸው የሙስና ክስ እልባት ሊሰጥበት እንደሚችልም ተገልጿል።
በዘንድሮው ምርጫ ድምጽ የሰጡ እስራኤላዊያን ዜጎች ከፈረንጆቹ 1999 ወዲህ ዝቅተኛ መራጮች የተሳተፉበት እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።