ታጣቂቹ ለገንዘብ ሲሉ ከፈረንጆቹ ታህሳስ 2020 ጀምሮ 1100 ተማሪዎችን አግተዋል
በሰሜን ናይጀሪያ ከሚገኘው ዛምፋራ ግዛት ውስጥ በተደረገ የጅምላ እገታ 73 ተማሪዎች መታገታቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ እንዳስታወቀው ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች በመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ ወረራ ፈጽመው እገታ ፈጽመዋል፡፡ ተማሪዎቹ የታገቱበት ዛምፋራ ግዛት ቃል አቀባይ ሞሀመድ ሸሁ ኮማንድ ፖስቱ ከወታደሩ ጋር የሚሰራ የፍለጋና የሚያድን ቡድን መላኩን ገልጸዋል፡፡
ታጣቂቹ ለገንዘብ ሲሉ ከፈረንጆቹ ታህሳስ 2020 ጀምሮ 1100 ተማሪዎችን ከ10 በላይ ከሆኑ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ማገታቸው ተገልጿል፡፡ ሮተርስ የናይጀሪያን
የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ የዛምፋራ ግዛት ተጨማሪ ጥቃቶችን ለመከላከል በማሰብ በግዛቱ ያሉት ሁሉም ት/ቤቶች እንዲዘጉ አዟል፡፡
ፖሊስ ጥቃቱን ለመከላከል ተጨማሪ የጸጥታ ሃይል ማሰማራቱንም ገልጿል፡፡ እገታው በተፈጸመበት ትምህርት ቤት 500 ተማሪዎች መመዝገባቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ዛምፋራ ሰሜን ናይጀሪያ ከሚገኙ 4 ግዛቶች አንዷ ስትሆን እገታን ለመከላከል እርምጃ እየወሰደች ትገናለች፡፡
በናይጀሪያ ሰሜናዊ ግዛት በተደጋጋሚ የታማሪዎች እገታ ይፈጽማል፡፡