የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ካን ባለቤት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ወደ እስር ቤት ተዛወሩ
ቡሽራ ቢቢ ለፍድር ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ባለስልጣናትን በቁም እስር እንዲቆዩ በተደረገበት ቤታቸው ገበናቸውን በመጣስ እና የተበከለ ምግብ በማቅረብ ከሰዋል
የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ባለቤት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ወደ እስር ቤት መዛወራቸውን ጠበቃቸው ተናግሯል
የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ባለቤት በፍላጎታቸው ወደ እስር ቤት መዛወራቸውን ጠበቃቸው ተናግሯል።
የፓኪስታን ፍርድ ቤት የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ከቁም እስር ወደ መደበኛ እስር ቤት ለመዛወር ያቀረቡትን ጥያቄ ረቡዕ ዕለት መቀበሉን ጠበቃቸው መናገሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
ቡሽራ ቢቢ ለእስላማባድ ከፍተኛ ፍድር ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ባለስልጣናትን በቁም እስር እንዲቆዩ በተደረገበት ቤታቸው ገበናቸውን በመጣስ እና የተበከለ ምግብ በማቅረብ ከሰዋል።
በአብዛኛው ወንዶች ናቸው የተባሉት የእስርቤት ሰራተኞች ግን ቢቢ ያቀረቡት ክስ ሀሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል።
ጥንዶቹ ለሀገር የተበረከተ ስጦታን በህገወጥ መንገድ በመሸጥ ባለፈዉ ጥር ጥፋተኛ ከተባሉ ጀምሮ ቢቢ በእስላማባድ ተራራ ላይ በሚገኘው የካን ቤት በአንድ ክፍል ውስጥ ታስረው ቆይተዋል።
ቢቢ ወደ እስር ቤት እዲዛወሩ ፍርድ ቤቱ ካዘዘ በኋላ ባለስልጣናቱ ወዲያውኑ መተግበራቸውን ፓርቲያቸው እና የአካባቢው አስተዳደር ባለስልጣን አፍዛል አህመድ ተናግረዋል።
ፓርቲው እንዳለው ቢቢ መታሰር ሲገባቸው በቤታቸው እንዳቆዩ የተደረገው ከመንግስት ጋር በተደረገ ድርድር ነው ሲሉ ለነበሩ ተችዎች መልስ የሚሰጥ ነው ብሏል።
የፓኪስታን ጦር ቃል አቀባይ ሜጄር ጀነራል አህመድ ሸሪፍ በትናንትናው እለት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት በሀገሪቱ ተቋማት ላይ ጥቃት ከፈጸመ ማንኛውም ፓርቲ ጋር ንግግር ማድረግ የሚቻል አይደለም ብለዋል።
ጀነራሉ ይህን ያሉት ባለፈው አመት ግንቦት ወር ወታደራዊ ተቋማትን ያጠቁትን የካን ደጋፊዎች ለማመላከት ነው። ይህን ጥቃት የፈጸሙ አካላት ድርድር ለማድረግ ከመጠየቃቸው በፊት ለፈጸሙት ድርጊት ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባቸው ጀነራሉ ገልጸዋል።
የካን የቅርብ ረዳት የሆነው አሳድ ቃይሳር አራይ ለተባለ ቴሌቪዥን እንደተናገረው የትኛውም አይነት ይቅርታ አይጠይቁም።
በ2022 ከስልጣን የተወገዱት ካን ጦሩ ሴራ ፈጽሞብኛል ሲሉ ይወቅሳሉ።