ኃላፊው እንዳሉት 40 የሚሆኑ አሸባሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት መደበቃቸውን እና እነዚህን ለመያዝ 400 ፖሊሶች እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል
የፖኪስታን ፖሊስ በላሆር የሚገኘውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን መኖሪያ ቤትን ለመበርበር ማቀዱን ገልጿል።
ይህ የፖሊስ እቅዱ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ አለመረጋጋት ውስጥ ባለችው ፖኪስታን አመጽ ሊቀሰቅስ እንደሚችል ሮይተርስ ዘግቧል።
የፑንጃብ ግዛት የመረጃ ኃላፊ አሚር ሚር በከተማዋ የፖሊስ ኮሚሽነር የሚመሩ በመቶ የሚቆጠሩ ፖሊሶች ምርመራውን ያካሂዳሉ ሲሉ ተናግረዋል።
ኃላፊው እንዳሉት 40 የሚሆኑ አሸባሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት መደበቃቸውን እና እነዚህን ለመያዝ 400 ፖሊሶች እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የካን ቤት በፑንጃብ ግዛት ላሆር በምትባል ከተማ ይገኛል።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን በፖሊስ ተይዘው ታስረው የነበረ ሲሆን በዋስ ከፍርድ ቤት ወጥተዋል።
ካን በፖሊስ የያዙት ለመንግስት የተበረከተ ስጦታን ሸጠው ለግላቸው አውለዋል በሚል ተጠርጥረው ነው።