ካሃን “ተቃዋሚዎቼ ከአሜሪካ ጋር እያሴሩ ሊገለብጡኝ ነው” ብለው ነበር
የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራን ካሃን በሀገሪቱ ፓርላማ የመተማመኛ ድምፅ በማጣታቸው ከስልጣን ተነሱ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን አመራር ላይ የመተማመኛ ድምጽ የመስጠትሂደት የተካሄደው እኩለ ሌሊት ላይ ሲሆን፤ ድምጽ የተሰጠው ተቃዋሚዎቻው በእርሳቸው ላይ ሞሽን ካቀረቡ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
የመተማመኛ ድምጽ እንዲሰጥ የሚጠይቀው ሞሽን ባሳለፍነው ሳምንት ቀርቦ የነበረ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ብላው ፓርላማውን በመበተናቸው ሳይካሄድ ቆይቶ ነበረ።
የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍድር ቤት ኢምራን ካሃን ከህገ መንግስቱ ውጪ ፓርላማውን በትነዋል በሚል ውሳኔያቸውን ውድቅ ማድረጉት ተክሎም ፓርላማው ተሰብስቦ ድምጽ ሰጥቷል።
ይህንን ተከትሎም ኢምራን ካሃን በፓርላማው የመተማመኛ ድምጽ በማጣታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው መነሳታቸው ታውቋል።
ኢምራን ካሃን በፓኪስታን ታሪክ የመተማመኛ ድምጽ በማጣት ከስልጣናቸው የተነሱ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናውም ተዘግቧል።
የፓኪስታን ፓርላማ ኢምራን ካሃንን ተክተው ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑትን ሰው ነገ ሰኞ እንደሚመርጥ ይጠበቃል።
በኢምራን ካሃን ቦታ የሚመረጠው ሰውም በሀገሪቱ ምርጫ እስከሚደረግበት የፈረንጆቹ ጥቅምት 2023 ድረስ በስልጣን ላይ የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን በትናትናው እለት “ተቃዋሚዎቼ ከአሜሪካ ጋር እያሴሩ ሊገለብጡኝ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሩሲያ በመሄዳቸው አሜሪካ ደስተኛ እንዳልሆነች ከዚህ ቀደም መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፤ አሜሪካ በፓኪታን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃእጠገባች ነው ያለችው ኢስላማባድ፤ ይህንን ተቃውሞዋን በይፋ ገልጻ ነበር።
ከሰሞኑ ኑሮ ውድነትን ሰበብ ባደረጉ ተቃውሞዎች ስትናጥ የከረመችው ፓኪስታን ይበልጥ እንዳትበጠበጥ በሚል ጥብቅ የጸጥታና ደህንነት ቁጥጥሮች እየተደረጉ መሆኑን የሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።