የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ አረፋ
ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ በ95 ዓመታቸው ማረፋቸውን ቫቲካን አስታውቃለች
ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ በፈረንጆቹ ከ2005 እስከ 2013 ለ8 ዓመታ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መርተዋል
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ አረፋ።
ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ፖፕ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ባደረባቸው ሕመም በዛሬው ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ማረፋቸውን ቫቲካን አስታውቃለች።
የወቅቱ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከቀናት በፊት ባወጡት መግለጫ፣ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ክፉኛ ሕመም ላይ መሆናቸውን ገልጸው ምእመኑ እንዲጸልያላቸው ጠይቀው ነበር።
የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ በፈረንጆቹ ከ2005 እስከ 2013 ለ8 ዓመታ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መርተዋል።
ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ በህመም ምክንያተ መልቀቂያ ማስገባታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህም በ600 ዓመታ ውስጥ መልቀቂያ ያስገቡ የመጀመረቲያው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳስ አድርጓቸዋል።
የቀድሞ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ኤሜራተስ በጀርመን በራቪያ ተወልደው ያደጉ ሲሆን፤ ቤኔዲክት 16ኛ በሚለው መጠሪያቸው ነው በስፋት የሚታወቁት።