ስፖርት
አራት የፒኤስጂ ተጨዋቾች በመሳደባቸው ምክንያት ተቀጡ
ኦስማን ደምበሌ፣ አሽራፍ ሀኪሚ፣ ራንዳል ኮሎ ማውኒ እና ሌቪን ኩርዛዋ ማርሴሌን 4-0 ከሸነፉ በኋላ ድላቸውን በሚያከብሩበት ወቅት ነበር ስድብ ያሰሙት
ፒኤስጂ ኮሚሽኑ ተመጣጣኝ እና ጥቅል የሆነ እርምጃ በመውሰድ የንግግርን እና የመከላከል ጥረትን የሚያዳክም ውሳኔ ማሳለፉ እንዳሳዘነው ገልጿል
አራት የፖሪስ ሴንት ጄርሜን(ፒኤስ) ተጨዋቾች በመሳደባቸው ምክንያት ቅጣት ተጣለባቸው።
የፈረንሳይ ሊግ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ባለፈው ወር ከተካሄደው የሊግ ጨዋታ በኋላ ተጨዋቾቹ በዋና ተቀናቃኛቸው ማርሲሌ ላይ ስድብ በመሰንዘራቸው አንድ ጨዋታ እንዲቀጡ (እንዳይሰለፉ) መወሰኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኦስማን ደምበሌ፣ አሽራፍ ሀኪሚ፣ ራንዳል ኮሎ ማውኒ እና ሌቪን ኩርዛዋ ክለባቸው ፒኤስጂ ማርሴሌን 4-0 ከሸነፈ በኋላ ድላቸውን በሚያከብሩበት ወቅት ነበር ስድብ ያሰሙት።
ይህን ተከትሎ ኮሚሽኑ አራቱን ተጨዋቾች ጠይቋቸው እንደነበር ተገልጿል። ተጨዋቾቹም ይቅርታ ጠይቀው ነበር።
በፖርክ ደስ ፕሪንሰስ በተካሄደው ጨዋታ ላይ ተወሰኑ የፒኤስጂ ደጋፊዎች የጸረ- ተመሳሳይ ፆታ ተቃውሞ ከፍ አድርገው በማሰማት ተጨማሪ ችግር ፈጥረው ነበር።
ፒኤስጂ ባወጣው መግለጫ ኮሚሽኑ ተመጣጣኝ እና ጥቅል የሆነ እርምጃ በመውሰድ የንግግርን እና የመከላከል ጥረትን የሚያዳክም ውሳኔ ማሳለፉ እንዳሳዘነው ገልጿል።