የሳኡዲ አረቢያው አል ሂላል ክሊያን ምባፔን ክብረወሰን በሰበረ 259 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቧል
ፖሪስ ሴንት ጀርሜን(ፒኤስጂ) አጥቂው ክሊያን ምባፔ ሊያስፈርመው ከፈለገው የሳኡዲ አረበያው አል ሂላል ጋር እንዲነጋገር መፍቀዱን ስካይ ነውስ ዘግቧል።
ፒኤስጂ ክሊያን ምባፔ እንዲገጋገር የፈቀደው አል ሂላል ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።
የሳኡዲ አረቢያው አል ሂላል ክሊያን ምባፔን ክብረወሰን በሰበረ 259 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቧል።
በቅርብ ቀናት ውስጥ ቶትንሃምን ጨምሮ ቢያንስ አምስት ክለቦች ምባፔን ለማስፈረም የፈረንሳዩን ክለብ ማናገራቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ለፒኤስጂ የቀረበለት ዋጋ ክብረወሰን የሰበረው የአል ሂላል ዋጋ ብቻ አይደለም። ፒኤስጂ ተጨዋች እና ገንዘብን ጨምሮ በርካታ ዋጋዎች ቀርቦለታል፤ ነገርግን አል ሂላል ክብረወሰን የሰበረ ዋጋ አቅርቧል።
ምባፔን ለማስፈረም ቸልሲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ኢንተርሚላን እና ባርሴሎና ፍላጎታቸውን አሳይተዋል።
ፒኤስጂ ምባፔን የተሻለ ክፍያ ላቀረበ የሚሸጠው ከሆነ ሌሎች ክለቦች አል ሂላል ወደአቀረበው ዋጋ መጠጋት ይኖርባቸዋል ተብሏል።
ከውድድር ዘመን ቀድም ብሎ ወደ ጃፖን እና ደቡብ ኮሪያ ከሚደረጉት ጉብኝቶች ውጭ ያደረገው ክለቡ የ24 አመቱን ምባፔን ለሽያጭ አቅርቦት ነበር።
ፒኤስጂ እንደገለጸው ለክለቡ ቁርጠኛ የሆነ ተጫዋቾችን ብቻ እንደሚያካትት ተናግሯል። ምባፔ ባለፈው ወር በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የሚያበቃውን ኮንትራቱን እንደማያድስ መግለጹን ተከትሎ በክለቡ እና በምባፔ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ገብቷል።
ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና ከስፔን በተጨማሪ በጣሊያን ያሉ ትላልቅ ክለቦች አጥቂውን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ተብሏል።
በነጻ የክረምት ዝውውር ሪያል ማድሪድን እንሚቀላቀል መስማማቱን ተከትሎ ከፒኤስጂ ጋር ያለው ኮንትራት ለማደስ ፍቃደኛ አልሆነም።
ምባፔ ከፒኤስጂ ጋር ያለው ኮንትራት አንድ አመት ነው የቀረው።
ተጨዋቹ ፒኤስጂን የተቀላቀለው በፈረንጆቹ 2017 ለአንድ የውድድር ዘመን የነበረ ቢሆንም ቆይቶ ቋሚ ሆኗል።