ከአራት ሳምንታትን በደፈነው የእስራኤል ሃማሰ ጦርነት ያሉ አዳዲስ ክስተቶች ምን ምንድናቸው?
እስራኤል በአምቡላንስና ትምህርት ቤቶች ላይ በወሰደችው እርምጃ ቢያንስ 50 ሰዎች ሞተዋል
አሜሪካ በእስኤልን ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ ተኩስ አቁም እንዲደርግ ጠይቃለች
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት የሰነዘረው ልክ የዛሬ አራት ሳምንት ቅዳሜ እለት ነበረ።
እስራኤልም ራሷን ለመከላከልና የአጸፋ እርምጅ ለመውሰድ ጋዛ ላይ ድብደባ ከጀመረች 28 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን በእስራኤል ጦርና በሃማስ ታጣቂዎች መካከል የተቀከቀሰው ጦርነትን እንደቀጠለ ይገኛል።
እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ ያደረሰ ሲሆን አምቡላንስ እና ሁለት ተፈናቃዮችን አስጠልለው የነበሩ ትምህርት ቤቶችም በእስራኤል የአየር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
በጋዛ ከተማ በአምቡላንስ ላይ በተፈጸመው ጥታት በጥቂቱ 15 ሰዎች መሞታቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስደተኞችን አስጠልለው በነበሩ ሁለት ትምህርት ቤቶች ላይ በተፈጸመው ጥቃትም በእያንዳንዳቸው የ14 እና የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ነው ባለስልጣናቱ ያስታወቁት።
በሰሜን ጋዛ በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጠቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፤ በተለይም በሰሜን ጋዛ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የእሰራኤል ጦር በጋዛ ከምታደርገው የመሬት ላይ ውጊያ በተጨማሪ በዌስት ባንክ ወረራ ማድረግ የጀመረች ሲሆን ጦሯ ናብለስ፣ ጄኒን፣ ሄብሮን እና ቤተሊሄም መግባታቸው ተነግሯል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ አሜሪካ ከእስራኤል ጋር መወያየቷን እና በጋዛ ታጋቾችን ለማስለቀቅ የተኩስ አቁም እንደሚያስፈልግ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባ በመቀነስ የምድር ውጊያ ላይ ልታተኩር እንደምትችልም የአሜሪካ ለስልጣናት አስታውቀዋል።
ጦርነቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ
እስራኤል በዌስት ባንክ ሌሊቱን በፈጸመችው የአየር ድብደባ 7 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል።
እስራኤል እየወሰደችው ባለው የአጻፋ እርምጃም ከ9 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ህይወት መቀጠፉን እና ከ32 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ማድረሱን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከሞቱ ሰዎች መካከልም ከ3 ሺህ በላይ ህጻናት፤ 2 ሺህ ደግሞ ሴቶች ናቸው ሲሆኑ፤ ከ20 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን ቆስለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር በጋዛ በየቀኑ ከ420 በላይ ህጻናት ይገደላሉ ወይም ይቆስላሉ ሲሉ አስታውቀዋል።
በእስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 400 ላይ ቆሟል።