በእስራኤል ሃማስ ጦርንት የተከሰቱ አዳዲስ ነገሮች ምንድናቸው? እስካን የምናውቀው…
እስራኤል አል-ቁዱስ ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሊቱን በጋዛ የአየር ድብደባ ፈጽማለች
በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 9 ሺህ ደርሷል 32 ሺህ ሰዎች ቆስለዋል
በሰሜን ጋዛ በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጠቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፤ በተለይም በሰሜን ጋዛ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ሃማስ እስራኤል ያልተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት በእግረኛ ጦር፣ በብረት ለበስ እና በአየር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ ያደረሰ ሲሆን አል ቁዱስ ሆስፒታል ቅጥር ጊቢ እና የስደተኞች ካምፖች ኢላማዎቹ ነበሩ።
በሰሜን ጋዛ በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጠቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፤ በተለይም በሰሜን ጋዛ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
እስራኤል በጀመረችው የምድር ውጊያ የተገደሉ ወታደሮች በትናናው እለት 4 ወታደሮቿ ተገድለውባታል፤ ይህንን ተከትሎም የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 23 መድረሱን አስታውቃለች።
እስራኤል የጋዛ ሰርጧን ትልቅ ከተማ መክበቧን እና ሀማስን ለማጥፋት በትኩረት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አስታወቀች።
የሄዝቦላህ መሪ ሃሳን ነስረላህ የአስራኤል ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
የኢራኑ አያቶላህ ሃመኒ እስራኤል ተስፋቢስና ግራ የተጋባች ሆናለች ለእስራኤላውያንም መንግስተችሁ በሃማስ ስለ ታገቱ ሰዎች ውሸት እየነገረ ነው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በአንድ ወር ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ወደ ዘእስራኤል አቅንተዋል።
ብሊንከን መጀመሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር በመቀጠል ከእስራኤል የጦርነት ጊዜ ካቢኔ ጋር ይነጋገራሉ።
ጦርነቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ
እስራኤል በዌስት ባንክ ሌሊቱን በፈጸመችው የአየር ድብደባ 7 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል።
እስራኤል እየወሰደችው ባለው የአጻፋ እርምጃም ከ9 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ህይወት መቀጠፉን እና ከ32 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ማድረሱን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከሞቱ ሰዎች መካከልም ከ3 ሺህ በላይ ህጻናት፤ 2 ሺህ ደግሞ ሴቶች ናቸው ሲሆኑ፤ ከ20 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን ቆስለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር በጋዛ በየቀኑ ከ420 በላይ ህጻናት ይገደላሉ ወይም ይቆስላሉ ሲሉ አስታውቀዋል።
በእስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 400 ላይ ቆሟል።