እስራኤል የጋዛ ከተማን መክበቧን አስታወቀች
የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ አራተኛ ሳምንቱን ሊያስቆጥ አንድ ቀን ሲቀረው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒዮ ብሊንከን ወደ እስራአል አቅንተዋል
በጋዛ የሚገደሉ ንጹሃን ሰዎች መጨመሩ የአለም መሪዎች ግጭቱ ይቁም የሚል ጥሪ እንዲያሰሙ አደርጓቸዋል
እስራኤል የጋዛ ከተማን መክበቧን አስታወቀች።
እስራኤል የጋዛ ሰርጧን ትልቅ ከተማ መክበቧን እና ሀማስን ለማጥፋት በትኩረት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አስታወቀች።
እስራኤል ይህን ያስታወቀችው አሜሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ላይ ጦርነቱን ጋብ እንዲል እና ወደ ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ጫና እያሳደረች ባለችበት ወቅት ነው።
የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ አራተኛ ሳምንቱን ሊያስቆጥ አንድ ቀን ሲቀረው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒዮ ብሊንከን ወደ እስራአል አቅንተዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ እስራኤል ሲያቀኑ በአንድ ወር ውስጥ ይህ ለሁለኛ ጊዜ ነው።
ጦሩ ጋዛን መክበቡን ካሳወቀ በኋላ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ "ከባድ ጦርነት ላይ ነን። አመርቂ ውጤት አምጥናል፣ የጋዛ ዳርቻ ቦታዎች አልፈናል። ወደፊት እየገሰገስን ነው።" ብለዋል
ብሊንከን በጋዛ ያሉ ንጹሃን ጉዳት መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገርግን ኃይት ኃውስ ሊደረግ የሚችል ተኩስ አቁም ካለ ጊዜያዊ እና እስራኤል ራሷን ከመከላከል የሚያግዳት ሲረጋገጥ መሆኑ ነው ብሏል።
በጋዛ እየተጠናከረ በመጣው ግጭት ምክንያት የሚገደሉ ንጹሃን ሰዎች መጨመሩ የአለም መሪዎች ግጭቱ ይቁም የሚል ጥሪ አብዝተው እንዲያሰሙ አደርጓቸዋል።
እስራኤል ግን ኢላማ ያደረኩት ሆነ ብለው በህዝብ ውስጥ የተደበቁትን የሀማስ ታጣቂዎችን ነው በማለት ጥሪውን እንደማትቀበለው ትገልጻለች።
ኃይት ኃውስም በተመሳሳይ የተኩስ አቁም ጥረን ውድቅ አድርጓል።
የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በጦርቱ ከተጀመረ አንስቶ 2.3 ሚሊዮን ህዝብ ባለባት ጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 9061 መድረሱን ገልጿል።
የተመድ ገለልተኛ ባለሙያዎች በጋዛ "የዘር ማጥፋት አደጋ አንዣቧል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ባለሙያዎቹ እስራኤል እና አጋሮቿ አስቸኳይ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የእስራኤል የጄኔቫ ተልእኮ ይህ የባለሙያዎቹ አስተያየት እንዳሳዘነው ገልጿል።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ ዘርማጥፋት ወይም ጄኖሳይድ የሚባለው በሚመለከተው የተመድ የህግ አካላት ነው ብለዋል።
በጥምቀት መጀመሪያ ሳምንት ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም 1400 ዜጎቿን የገደለባትን ሀማስ ከምድረ ገጹ ለማጥፋት ያለመችው እስራኤል፣ እየወሰደችው ያለው እርምጃ ራሷን የመከላከል እንደሆነ እየገለጸች ነው።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በጋዛ ተኩስ እንዳቆም እና የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ቢወስንም፣ እስራኤል ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል።