እስራኤል በሊባኖስ ድንበር በኩል በተጠንቀቅ ላይ መሆኗን ጦሩ ገለጸ
ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ላደረሰው ሀማስ አጋርቱን ለማሳየት ነበር ሄዝቦላህ በሰሜን እስራኤል ጥቃት የከፈተው
እስራኤል የጋዛ ሰርጧን ትልቅ ከተማ መክበቧን እና ሀማስን ለማጥፋት በትኩረት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አስታወቀች
እስራኤል በሊባኖስ ድንበር በኩል በተጠንቀቅ መሆኗን የእስራኤል ጦር ገልጿል።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት እስራኤል ከሊባኖስ ጋር በሚያዋስናት በሰሜን ድንበራ ላይ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ነች።
እስራኤል ይህን ያለችው የሊባኖሱ ሄዝቦላህ መሪ ዛሬ ምሽት ከሚሰጠው መግለጫ ቀድማ እና ቡድኑ በትናንትናው እለት 19 ሮኬቶችን በእስራኤላ ላይ መተኮሱን ከገለጸ በኋላ ነው።
ጥቅምት በመጀመሪያ ሳምንት ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ላደረሰው የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋርቱን ለማሳየት ነበር ሄዝቦላህ በሰሜን እስራኤል ጥቃት የከፈተው።
እስራኤል ከሄዝቦላ ጋር በሰሜን በኩል የተፋጠጠችበት ግንባር ጋዛን፣ ዌስትባንክን እንዲሁም ዘግይቶ ቀይ ባህርን ጨምሮ አራተኛው የውጊያ ግንባሯ ሆኗል።
እስራኤል የጋዛ ሰርጧን ትልቅ ከተማ መክበቧን እና ሀማስን ለማጥፋት በትኩረት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አስታወቀች።
የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ አራተኛ ሳምንቱን ሊያስቆጥ አንድ ቀን ሲቀረው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒዮ ብሊንከን እስራኤል ገብተዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ እስራኤል ሲያቀኑ በአንድ ወር ውስጥ ይህ ለሁለኛ ጊዜ ነው።
ጦሩ ጋዛን መክበቡን ካሳወቀ በኋላ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ "ከባድ ጦርነት ላይ ነን። አመርቂ ውጤት አምጥናል፣ የጋዛ ዳርቻ ቦታዎች አልፈናል። ወደፊት እየገሰገስን ነው።" ብለዋል።
ብሊንከን በጋዛ ያሉ ንጹሃን ጉዳት መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገርግን ኃይት ኃውስ ሊደረግ የሚችል ተኩስ አቁም ካለ ጊዜያዊ እና እስራኤል ራሷን ከመከላከል የሚያግዳት ሲረጋገጥ መሆኑ ነው ብሏል።
በጋዛ እየተጠናከረ በመጣው ግጭት ምክንያት የሚገደሉ ንጹሃን ሰዎች መጨመሩ የአለም መሪዎች ግጭቱ ይቁም የሚል ጥሪ አብዝተው እንዲያሰሙ አደርጓቸዋል።
እስራኤል ግን ኢላማ ያደረኩት ሆነ ብለው በህዝብ ውስጥ የተደበቁትን የሀማስ ታጣቂዎችን ነው በማለት ጥሪውን እንደማትቀበለው ትገልጻለች።
ኃይት ኃውስም በተመሳሳይ የተኩስ አቁም ጥረን ውድቅ አድርጓል።
የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በጦርቱ ከተጀመረ አንስቶ 2.3 ሚሊዮን ህዝብ ባለባት ጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 9061 መድረሱን ገልጿል።
የተመድ ገለልተኛ ባለሙያዎች በጋዛ "የዘር ማጥፋት አደጋ አንዣቧል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በጥምቀት መጀመሪያ ሳምንት ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም 1400 ዜጎቿን የገደለባትን ሀማስ ከምድረ ገጹ ለማጥፋት ያለመችው እስራኤል፣ እየወሰደችው ያለው እርምጃ ራሷን የመከላከል እንደሆነ እየገለጸች ነው።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በጋዛ ተኩስ እንዳቆም እና የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ቢወስንም፣ እስራኤል ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል።