ወጣቶቹ የሀገራቸው መንግስት በእስራኤል ላይ ማዕቀብ እንዲጥል የሚፈልጉ ናቸው ተብሏል
በብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖሪያ ግቢ ውስጥ ገብተው የተጸዳዱ ሰዎች ታሰሩ፡፡
በብሪታንያ በሚቀጥለው ሳምንት የጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን በሀገሪቱ ሁለት ወግ አጥባቂ እና ሊበራል ፓርቲ መካከል ፉክክሮች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን በስልጣን ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክን የሚቃወሙ ወጣች ወደ መኖሪያ ቤታቸው አምርተው ተቃውሟቸውን ገልጸዋል ተብሏል፡፡
ወጣቶቹ በለንደን በሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት በማቅናት ተጸዳድተዋል የተባለ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙት ደግሞ ለተቃውሞ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ አራቱንም ወጣቶች ወዲያውኑ በቁጥጥርሰ ር ማዋሉን የገለጸ ሲሆን ወጣቶቹ ለምን ድርጊቱን እንደፈጸሙት ሲጠየቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እስራኤል በጋዛ እያደረሰችው ላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እርምጃ አልወሰዱም በሚል መሆኑን ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ሱናክ አስተዳድር በእስራኤል ላይ ማዕቀብ እንዲጥል የሚጠይቁት እነዚህ ተቃዋሚዎች አዲስ የጋዝ ፈቃድ እንዳይሰጥ እና በተለይም በእስራኤል ላይ ጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣል ይፈልጋሉም ተብሏል፡፡
ከአንድ ሳምንት በኋላ በሚካሄደው የብሪታንያ ጠቅላላ ምርጫ በስልጣን ላይ ያሉት ሪሺ ሱናክ እና ከሰራተኞች ፓርቲ መሪው ኬር ስታርመር ጋር ከባድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
ብሪታንያ የኢትዮጵያ አበባ ያለ ግብር ወደ ሀገሯ እንዲገባ ፈቀደች
ፓርቲያቸው ወግ አጥባቂ ላለፉት 14 ዓመታት የህግ አውጪ ምክር ቤት መቀመጫዎችን በበላይነት በመያዝ በስልጣን ላይ ቆይቷል፡፡
በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ምክንያት በብሪታንያ ያጋጠመው የኑሮ ውድነት፣ የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ቀውስ እና ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷ የታሰበውን ያህል ጥቅም አለማስገኘቱ በስልጣን ላይ ላለው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ዋነኛ ፈተናዎች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚሁ ምርጫ ላይ ብርቱ ፉክክር እያደረገ ያለው የሰራተኞች ፓርቲ ከአንድ ሳምንት በኋላ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለይ አብላጭ ድምጽ ሊያገኝ እንደሚችል እና የፓርቲው መሪ ኬር ስታርመር ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው ሊመረጡ እንደሚችሉ ግምቶች እየወጡ ናቸው፡፡