የፈረንሳይ ጦር እስከ 2023 መጨረሻ ኒጀርን ለቀው እንደሚወጡ ፕሬዝዳንት ማክሮን አስታውቀዋል
ፈረንሳይ አምባሳሯን እና ጦሯን ከኒጀር ልታስወጣ መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አሳተወቁ።
ባለፈው ሐምሌ ወር መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን የተቆጣጠረው የኒጀር ጁንታ የፈረንሳይ አምባሳደር ስሊቪያን ሊቴ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙ ይታወሳል።
- ኒጀር የፈረንሳይ አምባሳደር በ48 ሰአታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች
- ስልጣን የተቆጣጠረው የኒጀር ወታደራዊ ቡድን የሩሲያው ዋግነር ቡድን እንዲረዳው ጠየቀ
በጁንታው የተሾመው የውጭ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ የፈረንሳይ አምባሳደር ለማባረር የተወሰነው ፈረንሳይ ከኒጀር ጥቅም በተቃራኒ በመቆሟ ነው ማለቱም ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ አምባሳደሬን አላስወጣም ስትል የቆየችው ፈረንሳይ አሁን ላይ ደግሞ አምባሳደሯን ከኒጀር ለማስወጣት መወሰኗን አስታውቃለች።
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ሀገራቸው በኒጀር የሚገኙትን የፈረንሳይ አምባሳደር እና ጦር ለማስጣት ከውሳኔ መድረሷን አስታውቀዋል።
ማክሮን አክለውም በኒጀር የፈረንሳይ አምባሳደርን ጨምሮ በርካታ ዲፕሎማቶች በሰዓታት ውስጥ ኒጀርን ለወቅ ይወጣሉ ሲሉ ተናግረዋል።
የፈረንሳይ ጦር እስከ 2023 መጨረሻ ኒጀርን ለቀው እንደሚወጡ ፕሬዝዳንት ማክሮን አስታውቀዋል።
ባለፈው ሐምሌ ወር በኒጀር የተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት በፈረንሳይ እና በኒጀር መካከል የነበረውን የቆየ ግንኙነት ወደ ከፋ ደረጃ አድርሶታል።