
አቃቤ ህግ የ33 እድሜ ያለውን የልጆቹን አባት በግድያ ወንጀል ምርመራ ከፍቶበታል
የፈረንሳይ ፖሊስ አራት ልጆቹን እና ባለቤቱን በመግደል የተጠረጠረ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አዋለ።
በፈረንሳይ ፖሊስ አራት ልጆቹን እና ባለቤቱን በቢላ ወግቶ ገድሏል የተባለውን ተጠርጣሪ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አቃቤ ህግ ገልጿል።
የማቾቹ አስከሬን ከፈረንሳይ ዋና ከተማ ፖሪስ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሞክስ ከተማ በደም በተጨማለቀ የአፖርትመት መኖሪያ ውስጥ የተገኘው ሰኞ እለት ነበር።
አቃቤህጉ እናትየዋ እና ሁለቱ ሴቶች ልጆች በርካታ ጊዜ በቢላዋ ተወግተዋል ብሏል።
የቤተሰቡ በእድሜ ትንሾቹ ሁለት ወንጆች ልጆች ታፍነው ተገድለው ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።
አቃቤ ህግ የ33 እድሜ ያለውን የልጆቹን አባት በግድያ ወንጀል ምርመራ ከፍቶበታል።
ልጆቹ ከ9 ወራት እስከ 10 አመት እድሜ ያላቸው ናቸው።
ጎረቤቶች የገና እለት ጠዋት የለቅሶ ድምጽ መስማታቸውን ለመርማሪዎች ተናግረዋል።መርማሪዎቹ እንደሚሉት ባልየው የአእምሮ ጤና ችግር ታሪክ ያለው ነው።
በ2029 በሚስቱ ላይ የቢላዋ ጥቃት ሰንዝሮ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ ባለቤቱ ክስ ባለማቅረቧ እና የአእምሮ ጤና ችግር እንዳለበት በመገለጹ ክሱ ወድቅ ተደርጎለት ነበር።
መርማራዎች በቤቱ ውስጥ የጸረ-ጭንቀት መድሃኒት አግኝተዋል።