በታዋቂው ራፐር ቱፖክ ግድያ የተጠረጠረ ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት
የሂፕ ሆፕ ኮከቡ ቱባክ በ25 አመቱ ነበር በትራፊክ መብራት በቆመት በፈረንጆቹ 1996 ግድያ የተፈጸመበት

በግድያው የተጠረጠረው ዴቪስ የቱፖክ የረጅም ጊዜ ተቀናቃኝ የሆነው ኦርላንዶ አንደርሰን አጎት ሲሆን ፖሊስም ለረጅም ጊዜ ሲጠረጥረው ቆይቷል
በ1996ቱ የታዋቂው አሜሪካዊ ራፐር ቱፖክ ሻኩር ግድያ የተጠረጠረ ግለሰብ በላስቬጋስ ክስ ተመስርቶበታል።
የሂፕ ሆፕ ኮከቡ ቱባክ በ25 አመቱ ነበር በትራፊክ መብራት በቆመት በፈረንጆቹ 1996 ግድያ የተፈጸመበት።
የሁልጊዜ ምርጥ ከሚባሉት ራፐሮች አንዱ የሆነው ቱፖክ ከ27 አመታት በፊት በ1996 በመስከረም ወር በኔቫዳ ከተማ የተፈጸመበት ግድያ አለምን ያነጋገረ ሆኖ ቆይቷል።
ነገርግን በግድያ የተጠረጠረ ሰው በወቅቱ አለመያዙ መርማሪዎችን ተስፋ ያስቆረጠ እና ህዝብንም ያስገረመ ክስተት ሊሆን ችሏል።
አሁን የኔቫዳ ግራንድ ጁሪይ የ60 አመቱን ዱዋኔ ወይም "ኬፍ ዲ" ዴቪስ አደገኛ መሳሪያ በመጠቀም ቱፖክን ገድሏል በሚል ጠርጥሮ ከሶታል።
የላስቤጋስ ሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፖርትመንት ሼሪፍ ኬቪን ማክ ማሂል የቱፖክ ቤተሰቦች ለ27 አመታት ፍትህ ሲጠብቁ ነበር ብለዋል።
ኬቪን ማክ ማሂል አክለውም "ይህ ምርመራ የጀመረው መስከረም 7፣1996 ነው። ገና አላለቀም" ሲሉ ተናግረዋል።
"ግባችን በቱፖክ ግድያ የተሳተፉችን ተጠያቂ ማድረግ ነው" ያለችው የቱፖክ እህት ሰኪዋ ሻኩር ክስ መመስረቱ ድል ነው ብላች።
ሰኪዋ እንደገለጸችው "ይህ ወሳኝ ወቅት ነው። በዚህ ጉዳይ የነበረው የ27 አመት ዝምታ አሁን በማህበረሰባችን ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው።"
በግድያው የተጠረጠረው ዴቪስ የቱፖክ የረጅም ጊዜ ተቀናቃኝ የሆነው ኦርላንዶ አንደርሰን አጎት ሲሆን ፖሊስም ለረጅም ጊዜ ሲጠረጥረው ቆይቷል።
አንደርሰን ራፐሩ በተገደለት ምሽት ቱፖክ እና ጓደኞቹ በተሳተፉበት ድብድብ ውስጥ መካፈሉን ፖሊስ በወቅቱ አረጋግጦ ነበር።
በወቅቱ በግድያው እጁ እንደሌለበት ያስተባበለው አንደርሰን ከሁለት አመት በኋላ ከዚህ ጉዳይ ጋር ግንኙት በሌለው ግድያ ህይወቱ አልፏል።
የሳውዝ ሳይድ ኮሞተን ክሪስፕ ጋንግ አባል የነበረው ዴቪስ ቀደም ሲል በተደረገለት ቃለ ምልልስ ለጥቃቱ ጥቅም ላይ ውላለች በተባለችው መኪና ውስጥ እንደነበር አምኖ ነበር።