ፖለቲካ
ፈረንሳይ በኒጀር ያለውን አምባሲዋን ልትዘጋ መሆኑ ተገለጸ
ፈረንሳይ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠዋል የምትላቸው የቀድሞ ፕሬዝደንት ባዙም ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ጫና ስታደርግ ቆይታለች
የኒጀር ጁንታ፣ ጎረቤት የሆኑት ማሊ እና ቡርኪናፋሶ እንዳደረጉት ሁሉ የፈረንሳይ አምባሳደር እና ወታደሮች እንዲወጡ ማዘዙ ይታወሳል
ፈረንሳይ በኒጀር ያለውን አምባሲዋን ልትዘጋ መሆኑ ተገለጸ።
ፈረንሳይ በኒጀር ጁንታ እግድ ምክንያት የዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት ያልቻለውን የኒጀር ኢምባሲዋን ላልተወሰነ ጊዜ ልትዘጋ እንደምትችል ለኢምባሲው ሰራተኞች የተጻፈው ደብዳቤ አመልክቷል።
በኒጀር እና በቀድሞ ቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ መካከል የነበረው ግንኙነት የሻከረው፣ ባለፈው ሀምሌ ወር ወታደሮች የሀገራቱን ፕሬዝደንት መሀመድ ባዙምን ከስልጣን ካስወገዱበት ጊዜ ጀምሮ ነው።
የኒጀር ጁንታ፣ ጎረቤት የሆኑት ማሊ እና ቡርኪናፋሶ እንዳደረጉት ሁሉ የፈረንሳይ አምባሳደር እና ወታደሮች እንዲወጡ ማዘዙ ይታወሳል።
ፈረንሳይ መጀመሪያ ላይ ትዕዛዙን ችላ ብለው የነበረ ቢሆንም ከአንድ ወር በኋላ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አምባሳደሩ እና ወታደሮቹ እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
በእግዱ ምክንያት የኢምባሲው ሰራተኞች ስራቸውን ለመስራት መቸገራቸውን በደብዳቤው ላይ ተገልጿል።
ፈረንሳይ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠዋል የምትላቸው የቀድሞ ፕሬዝደንት ባዙም ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ጫና ስታደርግ ቆይታለች።ነገርግን ይህ ፍላጎቷ ሳይሳካ ቀርቷል።