ፈረንሳያውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ የመጀመሪያ ዙር ድምጽ ሰጥተዋል
በምርጫው በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንና በቀኝ ዘመም እጩዋ ማሪን ሌ ፔን መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃል
በዚህ ምርጫ 48 ነጥብ 7 ሚልዮን ፈረንሳያውያን ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸው መረጃዎች ያሳያሉ
ፈረንሳያውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ የመጀመሪያ ዙር ድምጽ በመስጠት ላይ ናቸው።
ፈረንሳይ እያካሄደች ባለችው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን እየተወዳደሩ ባሉት ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና በቀኝ ዘመም ፖለቲካ አራማጇ ማሪን ሌ ፔን መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃልም ነው የተባለው።
በሩሲና-ዩከሬን ጦርነት የመሃል ሰው በመሆን ትልቁን የዲፕሎማሲ ሚና ለመጫወት ስራ በዝቶቻው የነበረውና ብዙም ያልተሳካለቸው ኢማኑኤል ማክሮን ፤ በምርጫ ዘመቻው ወቅት ብዙ ቅስቀሳ ሲያደረጉ አለመታየታቸው ከእንስቷ ተቀናቃኛቸው ከባድ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችልም ተጠብቋል።
በተቃራኒው ‘ለዘብተኛ’ ፖለቲከኛ ተደርገው የሚወደሱት የቀኝ ዘመም አስተሳሰብ መሪዋ ማሪን ሌ ፔን ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ጠንካራ ዘመቻ መምራት መቻላቸው የምርጫው ፉክክር ቀላል እንደማይሆን ተገምቷል።
ሌ ፔን ከማክሮን በተለየ መልኩ በሀገር ውስጥ ጉዳዮች ላይ፤ በተለይም አሁን የፈረንሳያውያን ቀዳሚ ጉዳይ የሆነውን “የመግዛት አቅምን ማሳደግ ላይ” ያተኮረ የምርጫ ዘመቻ አድርገዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ግን ”ማሪን ሌ ፔን በዘረኝነት ማኒፌስቶዋ" ህዝብን ስጋት ውስጥ እየከተተች ነው” ሲሉ አስጠንቅቋል።
መረጃዎች እንደሚያመላከቱት ከሆነ፤ በአንደኛው ዙር በቀላሉ እንደሚያሸንፉና ለሁለተኛ ጊዜ በመመረጥ ከ20 ዓመታት በኋላ የከጃክ ሺራክ ታሪክን ይደግማሉ ተብለው የተጠበቁት ኢማኑኤል ማክሮን፤ በምርጫው የነበራቸው መሪነት እየጠበበ መጥቷል።
በዚህም ሁለቱ ግንባር ቀደም ተወዳዳሪዎች ሚያዝያ 24 ወደ ሚካሄደው ሁለተኛው ዙር ያቀናሉ የተባለ ሲሆን፤ የፈረንሳይ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች የምርጫው ውጤት ልክ 12፡00 ሰዓት ላይ የመጨረሻውን ውጤት የሚተነብይ ይሆናል።
የአውሮፓ ምርምር ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ፍራንኮይስ ቡሴክ፤ ከመጀመሪያው ዙር በኋላ ያለው የሁለት ሳምንት ጊዜ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጿል።
"ከመጀመሪያው ዙር በኋላ የሚፈለገውን አቀማመጥ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ማየት በጣም ደስ ይላል" ያሉት ተመራማሪዋ "ሌሎች ፓርቲዎች አመራራቸውን በማሰባሰብ ምን ማድረግ እንዳለባቸውና ለመረጧቸው ምን እንደሚመክሩ መወሰን አለባቸው” ብለዋል።
ቦውክ “ምርጫው በፈረንሳይ ፖለቲከኞች ለተሰላቹ መራጮች አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በተለይም በሶስተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙት የግራ ዘመሙ እጩ ለሆ ዣን-ሉክ ሜሌንቾን የበለጠ አሳሳቢ ነው” ብለዋል።
"በሌፔን እና ከማክሮን መካከል ይደረጋል ተብሎ በሚታሰበው ውድድር፤ መራጮች ማክሮንን ብቻ በመውቀስ የሚታወቁትን ሜሌንቾን እንዲደግፉ የሚመክር ማን ነው?" ብለውም ጠይቋል ተመራማሪዋ።
በዚህ ምርጫ ከመራጮች መዘግየት ጋር ተያይዞ፤ ከፍተኛ የድምጸ ተአቅቦ ሪከርድ ይመጣል የሚል ግምታቸው ያስቀመጡት ተመራማሪዋ፤ ያለው አስደሳች አጨራረስ በሁለተኛው ዙር የበለጠ ተስትፎ እንደሚኖር የሚያመላክት ነው ብለዋል።
በዚህ ምርጫ 48 ነጥብ 7 ሚልዮን ፈረንሳያውያን ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።