ፈረንሳይ ጽንስ ማስወረድን ህገመንግስታዊ መብት አድርጋ አጸደቀች
በፈረንሳይ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት 80 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የጽንስ ማስወረድ ተግባር ህጋዊ እንዲሆን ይፈልጋሉ

ፈረንሳይ በትናንትናው እለት የጽንስ ማስወረድ መብትን በህገመንግስቷ ውስጥ በማካተት ከዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች
ፈረንሳይ ጽንስ ማስወረድን ህገመንግስታዊ መብት አድርጋ አጸደቀች።
ፈረንሳይ በትናንትናው እለት የጽንስ ማስወረድ መብትን በህገመንግስቷ ውስጥ በማካተት ከዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
የጽንስ ማስወረድን በህገመንግስቱ እንደመብት መካተት በርካታ የሴቶች መብት ተሟጋቾች በደስታ ሲቀበሉት፣ በጸረ-ማስወረድ ቡድኖች ደግሞ ከፍተኛ ነቀፌታ አጋጥሞታል።
በሁለቱ የፈረንሳይ ምክር ቤቶች የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በ780 አብላጫ ድምጽ እና በ72 ተቃውሞ መጽደቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
የጽንስ ማስወረድን የሚደግፉ አንቂዎች የምርጫው ውጤት ይፋ ከሆነ በኋሏ "የእኔ አካል የእኔ ምርጫ ነው" የሚል መፈክር አሰምተዋል።
የጽንስ ማስወረድ ከአሜሪካ እና ከሌሎች ሀገራት በበለጠ ሁኔታ በፈረንሳይ በስፋት ተቀባይነት ያለው ተግባር ነው። በፈረንሳይ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት 80 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የጽንስ ማስወረድ ተግባር ህጋዊ እንዲሆን ይፈልጋሉ።
"ለሁሉም ሴቶች መልእክት አስተላለፈናል፤ አካላቸው የራሳችሁ ነው። ስለእናንተ ማንም መወሰን አይችልም" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ገብኤል አታል ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት ለህግ አውጭዎች ተናግረዋል።
የፈረንሳይ ሴቶች በፈረንጆቹ 1974 ከወጣው ህግ ወዲህ ጽንስ የማስወረድ ህጋዊ መብት አላቸው። ህጉ በወቅቱ በብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር።
ነገርግን የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፈረንጆቹ 2022 ጽንስ ማስወረድን ህገመንግስታዊ መብት ያደረገውን ውሳኔ ከቀለበሰው በኋላ የሴቶች መብት ተሟጋቾች ፈረንሳይ ህገመንግስታዊ መብት በማድረግ የመጀመሪያዋ ሀገር እንድትሆን ጫና ፈጥረዋል።