ፈረንሳይ 2ሺ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን ልትልክ ነው ተባለ
ማክሮን ሩሲያ ዩክሬንን እንዳታሸንፍ ምዕራባውያን ሀገራት የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ አለባቸው ሲሉ መዛታቸው ይታወሳል
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን የምታደርገውን ጥቃት የቀጠለች ሲሆን በቅርቡ ወሳኟን አቭዲቪካ ከተማን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን ተቆጣጥራለች
ረንሳይ 2ሺ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን ልትልክ መሆኑን ሩሲያ እንደምታውቅ የሩሲያ የውጭ ኢንተሊጀንስ ሰርቪስ(ኤስቪአር) ዳይሬክተር ሰርጌይ ናሪሽክን ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ "የአሁኑ የሀገሪቱ አመራር ለተራ ፈረንሳያውያን ሞት አይጨነቅም። ለሩሲያ የሚደርሳት መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ ፈረንሳይ ተጠባባቂ ኃይል ለመላክ ተዘጋጅታለች። በመጀመሪያው ዙር የምትልከው 2ሺ ጦር ነው" ማለታቸውን ሮይተርስ የሩሲያውን ታሰ ጠቅሶ ዘግቧል።
- የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሩሲያ ላይ ለምን አመረሩ?
- ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት ለፈረንሳይ እንደነውር መታየቱ ማብቃቱን ፕሬዝደንት ማክሮን ተናገሩ
ዳይሬክተሩ እንደሚሉት ከሆነ እንዲህ አይነት ብዙ ቁጥር ያለው የፈረንሳይ ወታደር ከእይታ ውጭ አይሆንም በሚል ፍራቻ አድሮባቸዋል።
ወደ ዩክሬን ሊመጡ የሚችሉ የፈረንሳይ ወታደሮች የሩሲያ ጦር ዋነኛ ኢላማ እንደሚሆኑም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በዩክሬን ጉዳይ በፓሪስ በተደረገ ስብሰባ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤሌ ማክሮን የምዕራባውያን ወታደሮችን ወደ ዩክሬን ሊላኩ እንደማይችሉ በግልጽ አልተናገሩም።
ማክሮን ሩሲያ ዩክሬንን እንዳታሸንፍ ምዕራባውያን ሀገራት የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ አለባቸው ሲሉ መዛታቸው ይታወሳል።
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን የምታደርገውን ጥቃት የቀጠለች ሲሆን በቅርቡ ወሳኟን አቭዲቪካ ከተማን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን ተቆጣጥራለች።
ዩክሬን የምዕራባውያን ወታደራዊ ድጋፍ በአፋጣኝ በለመድረሱ ቦታዎቹን ለመልቀቅ መገደዷን መግለጿ ይታወሳል።
ምዕራባውያን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ከማቅረብ አልፈው ጦር የሚልኩ ከሆነ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ስትል ሩሲያ አስጠንቅቃለች።