ፖለቲካ
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ መግባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማክሮን ጋር "ፍሬያማ ውይይት" እንደሚያደርጉ ገልጸዋል
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ።
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ መግባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሬዝደንት ማክሮንን በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲቀበሏቸው የሚያሳይ ፎቶዎች በኤክስ አካውንታቸው አጋርተዋል።
ፕሬዝደንት ማክሮን በስድስት አመታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማክሮን ጋር "ፍሬያማ ውይይት" እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
"በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል። ክቡር ፕሬዚዳንት በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ፅኑ ነው"ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
የፈረንሳይ የአለም ቅርስ የሆኑትን የላሊበላ አብያተ ቤተክርስቲያናትን ለመጠገን የገንዘብ ድጋፍ ያደረገች ሀገር ነች።