ግሪንላንድን ወደ አሜሪካ እጠቀልላለሁ ለሚለው የትራምፕ አስተያየት አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ምን ምላሽ ሰጠች?
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂን ኖኤል ባሮት አሜሪካ ለ 600 አመታት ያህል የዴንማርክ አካል ሆና የቆየችውን የአርክቲኳን ደሴት ትወራለች ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል
"አሜሪካን በድጋሚ ትልቅ እናደርጋለን" የሚሉት ሪፐብሊካንን በመወከል ምርጫ ያሸነፉት ትራምፕ ከግሪንላንድ በተጨማሪ የፖናማ ቦይን የአሜሪካ ግዛት እንደሚያደርጉ ዝተዋል
የአውሮፓ ህብረት በሉኣዊ ድንበሩ ላይ የሚቃጣን ጥቃት እንደማይታገስ ፈረንሳይ ገለጸች።
አውሮፓ ህብረት ሉአላዊ ድንበሩን ሌሎች ሀገራት እንዲወሩት አይፈቅድም በማለት የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግሪንላንድን እጠቀልላለሁ ላሉት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው እለት ምላሽ ሰጥተዋል።
ትራምፕ አሜሪካ ግሪንላንድንና የፓናማ ቦይን የምትቆጣጠረው በወታደራዊ ወይም በኢኮኖሚያዊ አማራጭ ስለመሆኑ ተጠይቀው መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።
"አሜሪካ ግሪንላንድ ትወራለች ብዩ አስብ እንደሆነ ብትጠይቁኝ መልሴ፣ አይሆንም ነው። ነገርግን ጉልበት ያለው ይኖራል ወደሚለው ዘመን እየገባን ነው? እንደዚያ ከሆነ መልሴ አዎ ነው" ብለዋል ባሮት።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂን ኖኤል ባሮት አሜሪካ ለ 600 አመታት ያህል የዴንማርክ አካል ሆና የቆየችውን የአርክቲኳን ደሴት ትወራለች ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።
"የአውሮፓ ህብረት ማንም ቢሆን ሌላ ሀገር ሉአላዊ ግዛቱን እንዲያጠቃ ይፈቀዳል የሚል ጥያቄ እንደማይኖር ግልጽ ነው" ሲሉ ለፈረንሳይ ኢንርሬዲዮ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። "ጠንካራ አህጉር ነን" ብለዋል ባሮት።
ትራምፕ ከሁለት ሳምንት በኋላ በዓለ ሲመታቸውን ከመፈጸማቸው በፊት የሰጡት አስተያየት የመስፋፋት አጀንዳ ቅርጽ እንዲይዝ አድርጎታል።
"አሜሪካ ግሪንላንድ ትወራለች ብዩ አስብ እንደሆነ ብትጠይቁኝ መልሴ፣ አይሆንም ነው። ነገርግን ጉልበት ያለው ይኖራል ወደሚለው ዘመን እየገባን ነው? እንደዚያ ከሆነ መልሴ አዎ ነው" ብለዋል ባሮት።
ባሮት የአውሮፓ ህብረት መፍራት ወይም መስጋት የለበትም፣ ነገርግን መንቃት እና መጠንከር አለበት ብለዋል።
"አሜሪካን በድጋሚ ትልቅ እናደርጋለን" የሚሉት ሪፐብሊካንን በመወከል ምርጫ ያሸነፉት ትራምፕ ከግሪንላንድ በተጨማሪ በማዕከላዊ ደቡብ አሜሪካ የሚገኘውን የፓናማ ቦይን የአሜሪካ ግዛት እንደሚያደርጉ ዝተዋል።
ትራምፕ ጎረቤት ካናዳንም የአሜሪካ 51ኛ ግዛት ሆና እንድትጠቃለል እንደሚፈልጉ መናገራቸው ይታወሳል።