ኪሊያን ምባፔ በፈረንሳይ እየተካሄደ ያለው ብጥብጥ እንዲያቆም ጠየቀ
በፈረንሳይ የ17 ዓመት ታዳጊ በትራፊክ ፌርማታ ከተገደለ በኋላ አለመረጋጋት ተከስቷል
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እና የፒኤስጂ ክለብ ተጫዋቹ ምባፔ "ሰላማዊ እና ገንቢ" ተቃውሞ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል
ምባፔ በፈረንሳይ እየተካሄደ ያለው ብጥብጥ እንዲያቆም ጠየቀ፡፡
የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አምበል ኪሊያን ማባፔ የ17 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ በሀገሪቱ የተነሳው ነውጥ መቆም አለበት ብሏል።
የ17 ዓመቱ ናሄል ኤም ባለፈው ማክሰኞ በትራፊክ ፌርማታ ሲያሽከረክር በፖሊስ ከተገደለ በኋላ ፈረንሳይ መረጋጋት ርቋታል።
ምባፔ በማህበራዊ የትስስር ገጹ "ግጭት ምንም የሚፈታው ነገር የለም" ብሏል።
የ24 ዓመቱ ወጣት ተጫዋች ክሊያን ምባፔ "ሰላማዊ እና ገንቢ" ተቃውሞ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
የፈረንሳይ መንግስት ሁከቱን ለመቆጣጠር 45 ሽህ የፖሊስ አባላትን እንደሚያሰማራ አስታውቋል።
ፈረንሳይ በደቡብ አፍሪካው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጠየቀች
የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የፊት መስመር ተጫዋች ምባፔ መግለጫ የፈረንሳይ ቡድንን ወክሎ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
"ልክ እንደ ሁሉም ፈረንሳውያን በወጣት ናሄል ሞት ደንግጠናል" ብሏል።
ምባፔ እንዳለው ብዙዎቹ እንደ ናሄል ካሉ ሰፈሮች የመጡ የፈረንሳይ ተጫዋቾች "የሀዘን እና የህመም ስሜቱን" ይጋራሉ በማለትም ገልጿል።
ምባፔ ያደገው በፓሪስ ሰሜን ምስራቅ በምትገኝ ቦንዲ ከተማ ሲሆን ገና በወጣትነቱ የሀገሪቱን ብሐየራዊ ቡድን በአምበልነት እየመራ ይገኛል።
ተጫዋቾቹ "የሀዘን፣ የውይይት እና የመልሶ ግንባታ ጊዜ እንዲሰጥ" ጠይቋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ የህዝብ ተቃውሞዎችን ያስተናገደችው ፈረንሳይ የአሁኑ ክስተት ከመከሰቱ በፊት የጡረታ ጊዜ መራዘምን በመቃወም አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር፡፡
እንዲሁም ፈረንሳይ የቢጫ መለዮ ለባሾች ሰልፍ፣ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ህግ ተቃውሞ እና ሌሎችንም ተቃውሞዎች አስተናግዳለች፡፡