እስራኤል በአየር ሃይል የበላይነቱን ስትይዝ በእግረኛ ጦርና በባህር ሃይል ኢራን ትበልጣለች
ኢራን በፈረንጆቹ 1948 ለተመሰረተችው እስራኤል እውቅና ከሰጡ ሙስሊም ከሚበዛባቸው ሀገራት ሁለተኛዋ ናት፤ ከቱርክ በመቀጠል።
ከእስራኤል ምስረታ በፊት ጀምሮ የፍልስጤም ጉዳይን በትኩረት የምትመለከተው ቴህራን እስከ 1979 ድረስ ከቴል አቪቭ ጋር ግንኙነቷ ቀጥሎ ነበር።
የኢራን አብዮት ግን እስራኤል እና የሚደግፏትን ምዕራባውያን “ጠላት” አድርጎ” መነሳቱ ይነገራል።
ባለፉት ሶስት አስርት አመታትም ሁለቱ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለጦርነት የሚፈላለጉና በእጅ አዙር የሚፋለሙ ባላንጣ ሆነዋል።
ኢራን ለሰላማዊ አላማ እጠቀመዋለው የምትለው የኒዩክሌር ሃይል ልማት ስጋት ውስጥ የከተታቸው አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት እስራኤልን በየአመቱ በቢሊየን ዶላሮች እየደገፉ ጠንካራ ወታደራዊ አቅም እንድትገነባ አግዘዋታል።
በህዝብ ብዛት ከእስራኤል በአስር እጥፍ ገደማ የምትልቀው ኢራንም ቴል አቪቭን ሊገዳደር የሚችል ሰራዊት በመገንባትና የጦር መሳሪያዎቿን በማዘመን ከተጠመደች አመታት ተቆጥረዋል።
የ145 ሀገራትን ወታደራዊ አቅም ደረጃ እና ዝርዝር መረጃዎች ይፋ ያደረገው ግሎባል ፋየር ፓወር ኢራንን 14ኛ፤ እስራኤልን ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል።
እስራኤል በአየር ሃይል የበላይነቱን ስትይዝ በእግረኛ ጦርና በባህር ሃይል ኢራን ትበልጣለች።
የሀገራቱን የ2024 ወታደራዊ ጥንካሬ በንጽጽር ምን እንደሚመስል በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦