ፈረንሳይ የፕሬዝዳንት ፑቲን የቀድሞ ሚስት ንብረትን አገደች
ሱዛና የምትባለው የቀድሞ ቭላድሚር ፑቲን ሚስት ንብረት የሆነ ቅንጡ መኖሪያ ቤት መታገዱ ተገልጿል
ፈረንሳይ በሀገሯ የሚገኘውን ይህን ቅንጡ መኖሪያ ቤት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ እገዳ ጥላለች
ፈረንሳይ የፕሬዝዳንት ፑቲን የቀድሞ ሚስት ንብረትን አገደች፡፡
በቅጽል ስሟ ሱዛና በመባል የምትታወቀው ሩሲያዊት የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቀድሞ ሚስት ናቸው፡፡
እኝህ እንስት አርቲር ኦክሬትኒ የተባለ ነጋዴ ጋር የፍቅር ግንኙነት መስርተው በፈረንሳይ በመኖር ላይ ነበሩ፡፡
በፈረንሳይ የወደብ ከተማ በሆነችው አንግሌት ከተማ በሚገኘው ቅንጡ መኖሪያ ቤታቸው የሚኖሩት እነዚህ ሩሲያዊያን ቤታቸው እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ መታገዱ ተገልጿል፡፡
ጥንዶቹ የአሁኑን ቤት በፈረንጆቹ 2013 ላይ በ5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዩሮ ከገዙት በኋላ ለእድሳት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሮ ወጪ አድርገውበታል ተብሏል፡፡
ይሁንና ይህ ቅንጡ ቤት ወጪ የተደረገበት ገንዘብ በህጋዊ መንግድ የተገኘ አይደለም በሚል ጥርጣሬ የፈረንሳይ ፖሊስ በቤቱ ላይ እገዳ እንደጠላ ተገልጿል፡፡
ከአምስት ወራት በፊት እገዳ የተጣለበት ይህ ቤት ከሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳለም በዘገባው ለይ ተጠቅሷል፡፡
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ የፈረንሳይ መንግስትን እርምጃ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡
የ21ኛው ክፍለ ዘመን ተጽዕኖ ፈጣሪ መሪ - ቭላድሚር ፑቲን
ፈረንሳይን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት በሩሲያዊያን ለይ የተለያዩ ማዕቀቦችን እና በየሀገራቸው ያሉ የሩሲያዊያንን ንብረቶች አግደዋል፡፡
ሩሲያም የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ ስትሆን በሀገሯ ያሉ የምዕራባዊያንን ንብረቶች ልትወርስ እንደምትችል አስጠንቅቃለች፡፡
ምዕራባዊን ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው የሩሲያዊያን ገንዘብ እና ንብረቶችን ያገዱ ሲሆን እነዚህን ሀብቶች ለዩክሬን መልሶ ግንባታ እንዲውሉ መንገዶን እያዩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያም የሩሲያዊያንን መንግስት እና ዜጎች ንብረት ለዩክሬን እንዳይሰጡ እና ይህን ካደረጉ ከባድ ጉዳት ይጠብቃቸዋል ስትል አስጠንቅቃለች፡፡