ፈረንሳይ በአንድ የፓርላማ አባል ላይ የዘረኝነት ጥቃት የሰነዘረን የምክር ቤት አባል ከስራ አገደች
ግለሰቡ ለ15 ቀናት ከስራ እና ደመወዝ መታገዱ ተገልጿል
የምክር ቤቱ አባል "ወደ አፍሪካ ተመለስ" ሲል በአንድ ጥቁር የፓርላማ አባል ላይ ጥቃት ሰንዝሯል
ፈረንሳይ በአንድ የፓርላማ አባል ላይ የዘረኝነት ጥቃት የሰነዘረን የምክር ቤት አባል ከስራ አገደች።
በፈረንሳይ ከትናንት በስቲያ በተካሄደ የምክር ቤት ስብስባ ላይ አንድ ጥቁር ፈረንሳዊ የሀገሪቱ መንግስት ለስደተኞች ትኩረት እንዲሰጥ በመናገር ላይ እያለ ንግግሩ ተቋርጧል።
ግሪጎሪ ደ ፎርናስ የተሰኘው ይህ ነጭ ፈረንሳዊ ጥቁር ፈርንሳዊ ዩሆነው የምክር ቤት አባል የፈረንሳይ መንግስት ከአፍሪካ በሚመጡ ስደተኞች ዙሪያ ንግግር እያደረገ እያለ "ወደ አፍሪካህ ተመለስ" ሲል በሀይለቃል መናገሩን ፍራንስ 24 ዘግቧል።
ንግግሩን ተከትሎ በመላው ፈረንሳይ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን የሀገሪቱ ምክር ቤትም የዘረኝነት ጥቃት በሰነዘረው የምክር ቤት አባል ላይ ቅጣት ጥሏል።
ግለሰቡ ለ15 ቀናት በምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳይካፈል እና የ15 ቀናት ደመወዙን ተቀጥቷል ተብሏል።
የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲን ወክሎ በሀገሪቱ ምክር ቤት የተገኘው ይህ ነጭ ፈረንሳዊ ለድርጊቱ ይቅርታ ጠይቋል።
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ድርጊቱን ኮንነው ማሪን ለፐን የሚመሩት የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ ውጤት ነው ሲሉም ተችተዋል።
በፈረንሳይ ፓርላማ ታሪክ የዘረኝነት ጥቃት ሲሰነዘር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በፈረንጆቹ 1958 ተመሳሳይ የዘረኝነት ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበር ተገልጿል።
በአውሮፓ ስደተኞችን የሚጠሉ ፖለቲከኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ሲገለጽ ጀርመን ፣ፈረንሳይ እና ስዊድን በስፋት የሚታይባቸው ሀገራት ናቸው።