ጀርመንና ፈረንሳይ “የሩሲያ ቱሪስቶችን ቪዛ ለመከልከል የቀረበውን ምክረ ሃሳብ” ተቃወሙ
ጆሴፕ ቦሬል “ሁሉም ሩሲያውያን ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ መከልከል ጥሩ ሀሳብ አይደለም” ብለዋል
ሀገራቱ፤ የአውሮፓ ፖሊሲዎች በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ቢያተኩሩ የተሻለ ነው ብለዋል
የአውሮፓ ህበረት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሩሲያ ዜጎችን የጉዞ ፈቃድን ለመገደብ በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መወያየታቸው እየተነረ ነው።
ለዚህም ህብረቱ ከሞስኮ ጋር ያለውን የቪዛ ስምምነት ለማቆም ከሚያስችል ውሳኔ ለመድረስ መዘጋጀቱን ኤ.ኤፍ.ፒ የዲፕሎማቲክ ምንጮቹን መረጃ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
ያም ሆኖ ምክረ ሃሳቡ ኃሳቡ በአንድ አንድ ሀገራት የህብረቱ ሀገራት ተቀውሞ እየገጠመው ሲሆን፤ ጀርመን እና ፈረንሳይ “ሩሲያውያን ቱሪስቶች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ ቪዛ ለመከልከል የቀረበውን ምክረ ሃሳብ” ተቃውሞውታል፡፡
ሀገራቱ ባወጡት የፍራንኮ-ጀርመን ሰነድ እንዳመላከቱት “የአውሮፓ ህብረት የሩስያ ቱሪስቶችን አውሮፓን ከመጎብኘት ሊከለክል አይገባም” ብለዋል።
"በዚህ አውድ ውስጥ የአንዳንድ አባል ሀገራትን ስጋት የምንረዳ ቢሆንም፤ በዴሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ ህይወትን የመኖርና የማጣጠም ትርጉም አቅልለን ማየት የለብንም" ሲሉም አክለዋል።
“የእኛ የቪዛ ፖሊሲዎች ማንጸባረቅ ያለባቸው ከሩሲያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ሳይሆን ከሩሲያ ዜጎች ጋር ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ነው” ብለዋል ሀገራቱ ባወጡት ሰነድ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል፤ ወደ አውሮፓ ህብረት የሚገቡ የሩሲያ ተጓዦች ላይ ሙሉ በሙሉ እገዳን ተግባራዊ ለማድረግ የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ አድርገውታል።
ቦሬል ሁሉም ሩሲያውያን ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ መከልከል "ጥሩ ሀሳብ አይደለም"ምብለዋል።
ያም ሆኖ ፤እንደ ኢስቶኒያ እና ፊንላንድ ያሉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሩሲያ ቱሪስቶች ላይ ቪዛን ለመገደብ የሚያስችሉ እርምጃዎች ቀደም ሲል መውሰድ መጀመራቸው የሚታወቅ ነው።