የማክሮን ጉብኝት በፈረንሳይና በአልጄሪያ መካከል ያለውን የግንኙነት መሻከር ለማሻሻል ያለመ ነው
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አልጀሪያን ሊጎበኙ መሆኑ ተሰምቷል።
ፕሬዝዳንቱ ከአንድ ወር በፊት ሶስት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራትን ጎብኝተው የተመለሱ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ሰሜን አፍሪካ አቅንተው አልጀሪያን እንደሚጎበኙ ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ከፈረንጆቹ ነሀሴ 25 አንስቶ ለሶስት ቀናት አልጀሪያን ይጎበኛሉ ተብሏል።
የፕሬዝዳንት ማክሮን ጉብኝት ከፈረንሳይ ጋር ግንኙነቷ የሻከረችው አልጀሪያን በመጎብኘት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ማክሮን በፈረንጆቹ 2017 ላይ አልጀርስን የጎበኙ ሲሆን የአሁኑ ጉዟቸው ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚሆን ዘገባው ጠቁሟል።
አልጀሪያ እና ፈረንሳይ ባሳለፍነው ዓመት ከቅኝ ግዛት ጊዜዎች ጋር በተያያዙ የታሪክ ሰነዶች ዙሪያ በተነሳ ውዝግብ ግንኙነታቸው የሻከረ ሲሆን ፈረንሳይም በአልጀርስ የነበሩ አምባሳደሯን ወደ ፓሪስ ጠርታለች።
አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ገለልተኛ መሆኗን ተከትሎ ምዕራባዊያን ሀገራት ደስተኛ ያልሆኑ ሲሆን አፍሪካ እንደ አህጉር ሩሲያን እንድታወግዝ በመወትወት ላይ ናቸው።
ፕሬዝዳንቱ ከአንድ ወር በፊት ምዕራብ አፍሪካ ሀገራትን በጎበኙበት ወቅት አፍሪካዊያን በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ላይ ተለሳልሰዋል ሲሉ መተቸታቸው ይታወሳል።