የኤችአይቪ ቫይረስን ከሌሎች ጋር በጋራ ያገኙት ፈረንሳያዊ ሳይንቲስት አረፉ
ሳይንቲስቱ ኮሮና ቻይና ነው የፈጠረው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸው ነበር
የ89 ዓመቱ ሞንታግኒየር ቫይረሱን በማግኘቱ ረገድ ላደረጉት ሚና በፈረንጆቹ በ2008 የኖቤል ሽልማት ከሌላ ፈረንሳያዊ ሳይንቲስት ጋር ተጋርተዋል
የኤችአይቪ ቫይረስ የሚያመጣውን ሁማን ኢሚውኖዲፊሺየንሲ ቫይረስ ያገኙትና የኖቤል ተሸላሚ የነበሩት ፈረንሳያዊው ቫይሮሎጂስት ሉክ ሞንታግኒየር ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የ89 ዓመቱ ሞንታግኒየር ቫይረሱን በማግኘቱ ረገድ ላደረጉት ሚና በፈረንጆቹ በ2008 ከተሰጠው የኖቤል ሽልማት ግማሹን ከፈረንሳዊው ሳይንቲስት ፍራንሷ ባሬ-ሲኑሲ ጋር አጋርተዋል። የቀረው ግማሸ ለጀርመናዊው የካንሰር ተመራማሪ ሃራልድ ዙር ሃውሰን ተሸልሟል።
በፈረንጆቹ 2020 ውዝግብ ያስነሳው ሞንታግኒየር ኮሮናቫይረስ የተፈጠረው በቻይና ቤተ ሙከራ ነው ብሎ አምናለሁ በማለት ውዝግብ አስነሰተው ነበር፡፡
በፓሪስ ዩኒቨርሲቲ በቫይሮሎጂ የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙት ሞንታግኒየር በፓሪስ የዓለም የኤድስ ምርምር እና መከላከል ፋውንዴሽን ዳይሬክተር መሆን አገልግለው ነበር፡፡
የኤድስ ወረርሽኝ ከመጀመሩ በፊት በነበሩት ዓመታት ሞንታግኒየር ስለ ቫይረሶች ምንነት ጠቃሚ የሆኑ ጥናቶች አድርገዋል፤ቫይረሶች የነፍሳት ህዋሳትን የዘረመል መረጃ እንዴት እንደሚለውጡ ለመረዳት አስተዋፅዖ አድርጓል።