በፈረንጆቹ 2030 ከኤችአይቪ ኤድስ ነጻ የሆነች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው ብሏል ጽ/ቤቱ
ጽ/ቤቱ ሀገር አቀፍ የኤች አይ ቪ ስርጭት መጠን 0.93 በመቶ መሆኑን ገልጿል
ተመድ በፈረንጆቹ 2030 የተያዙት የልማት አጀንዳዎች እንዲሳኩ አባል ሀገራት በሽታውን በ2030 ለማጥፋት ቁርጠኛ መሆን አለባቸው ብሏል
በፈረንጆቹ 2030 ከኤች አይ ቪ ነፃ የሆነች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠርያ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡
የፅ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳዳሬክተር አቶ አብርሀም ገ/መድህን ለአል-ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት የተያዘውን ግብ ለማሳካት ከ2021 እስከ 2025 የሚተገበር አዲስ እቅድ ተዘጋጅቶ ለተፈጻሚነቱ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡
አቶ አብርሀም እንደገለጹት ከእርጉዝ እናት ወደ ህፃን ቫይረሱ እንዳይተላለፍ የላቀ ትኩረት ለሚያደርጉ ስትራቴጅዎች ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል፡፡
ተመርምረው ቫይረሱ በደማቸው የተገኘባቸው ወገኖችም ወድያውኑ የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት እንዲጀምሩ፣ በደማቸው ውስጥ የሚገኘውን ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ እና ጤንነታቸውን ተጠብቆ እንዲሄድ የሚያደርጉ አሰራሮች እንደደሚተገበሩም ጭምር፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ622 ሺ በላይ ወገኖች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል የሚሉት አቶ አብርሀም አስካሁን በተሰራ ስራ ኤች አይ ቪ ኤድስ በመቆጣጠር እና በመከለከል ዙርያ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡ኢትዮጽያ አሁን ላይ ወረርሺኙን መቆጣጠር ከሚችሉ ሀገራት ተርታ እንደምትገኝም እንዲሁ፡፡
ሀገር አቀፍ የስርጭት መጠን 0.93 በመቶ መሆኑና ይህም ከክልል ክልል እንደሚለያይም ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አብርሀም ገ/መድህን የገለፁት።
የስርጭቱ መጠኑ ከፍተኛ መጠን ባለው የጋምቤላ ክልል 4.45% ፣ከዛ ቀጥሎም አዲስአበባ 3.42%፣ ድሬዳዋ 3.12%፣ ሃረር 2.97%፣ትግራይ 1.43%፣ አማራ 1.28%፣ አፋር 1.04%፣ ቤንሻንጉል 0.86%፣ ኦሮምያ 0.65%፣ ደቡብ ህዝቦች 0.45%፣ እንዲሁም ሶማሌ ክልል 0.16% መሆኑም አቶ አብርሀም እንደ አብነት አንስቷል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ “ሴተኘ አዳሪዎች፣ ትዳር የፈቱ ሴቶች፣ የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች እና ተንቀሳቃሽ የግንባታ፣ የማዕድን እና አበባ ምርት ሰራተኞች ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑና ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ተብለው የተለዩ ናቸው”ም ብለዋል:: ከነዚህ 90 በመቶ የሚሆቡት ወጣት ልጃገረዶች እና ወጣት ሴቶች መሆናቸውም ጭምር፡፡
በኢትዮጵያ በቀን በአማካኝ 30 ሰዎች በኤድስ ህይወታቸው ያጣሉ እንደሚቱ እንዲሁም ከ11 ሺ በላይ አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚያዙ የጸ/ቤቱ መረጀዎች ያመለክታሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) “ያለመመጣጠን ወረርሽን”ሲል የገለጸው ኤችአይቪ ኤድስን ለማስጥፋት የተመድ አባል ሀገራት ኢፍትሃዊነት እንዲቆም በስራት አለባቸው ብሏል፡፡ ተመድ የ2030 የዘላቂ ልማት ግብ እንዲሳካ ከተፈለገ፣በሽታውን በፈረንጆቹ 2030 እንዲጠፋ ሁሉም አባል ሀገራት ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡