በኬንያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒት እንዲለቀቅላቸው መንግስትን ጠየቁ
በኬንያ የፀረ ኤችአይቪ ቫይረስ መድኃኒቶች እጥረት በማጋጠሙ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ህመምተኞቹ በተቃውሞ ሰልፎች በመንግስት ላይ ጫና ማሳደር ጀምረዋል ፡፡
ሰልፈኞቹ ቲሸርት ለብሰው “የታመመ ህዝብ የሞተ ህዝብ ነው” ፣ “ገዳይ መንግስት” እና “ፀረ ኤችአይቪ ቫይረስ መድኃኒቶች(ARVs) ይለቀቁልን” የሚሉ መፈክሮችን የያዘ ፖስተር ይዘው ነበር፡፡
በጉምሩክ መጋዘኖች ተይዘው የነበሩትን መድኃኒቶች መንግሥት እንዲለቀቅላቸውም ነው ሰልፈኞቹ መንግስትን እየጠየቁ ያሉት፡፡
እንደ አሶሼስትድ ፕሬስ ዘገባ ከሆነ፤ በዚህ ዓመት የኬንያ የግብር እና የገቢ ባለሥልጣናት ለጋሽ ድርጅቶች መሚለግሷቸው መድሀኒቶች ላይ ግብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸው ተከትሎ ለጋሾቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ ይህ ለመድኃኒት አቅርቦት እጥረት መነሻ መሆኑም ጭምር፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቦኒፌስ ኦጉቱ አካች “136,000 የሚሆኑ የኤች.አይ.ቪ ታማሚ ሰዎች በኪሱሙ ይኖራሉ፤ይህ ማለት የአጠቃላይ ህዝባችን 13 በመቶ የሚሆነው እንደማለት ነው፤ ዝም ብለን ዝም ብለን ማየት አንችልም:: ይህ የሆነው ታማሚዎቹ በአንድ ቦታ ተኝተው መድሃኒት ማግኘት ባለመቻላቸው እና በመንግስት ነው ፤ ምክንያቱም መንግስት ለጋሽ ድርጅቶችን ግብር እንዲከፍሉ ይፈልጋልና” ሲሉም ነው የችግሩ መንስኤ የገለፁት፡፡
ኬንያ በአለም ዙርያ ካሉ ለጋሾች ለአብነትም እንደ የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት /ዩኤስኤአይዲ/ ከመሳሰሉ ድርጅቶች የፀረ-ኤች አይ.ቪ መድሀኒቶች ትቀበላለች ፡፡