ክሃን በቅርቡ በሀገር ክህደት ተከሰው በነበሩት አጋራቸው ላይ የፈረዱትን ዳኛ በማስፈራራት ነው የተከሰሱት ተብሏል
የቀድሞው የፓኪስታን ፕሬዝደንት ኢምራን ካህን ፍርድ ቤትን በመናቅ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡
የፓኪስታን ፍርድ ቤት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ላይ ክስ እንደተመሰረተበት ጠበቃው እና የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ኢምራን ክሃን በውሳኔ ላይ ምን ስሜት እንዳለው ተጠይ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልነበሩም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ክሃን በቅርብ በሀገር ክህደት ተከሰው በነበሩት አጋራቸው ላይ የፈረዱትን ዳኛ በማስፈራራት ነው የተከሰሱት ተብሏል፡፡
ጠበቃው ፋይሰል ቻውድሪ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ፍርድ ቤቱ ክስ ለመመስረት ወስኗል። በአምስት አባላት ዳኞች የተላለፈ ውሳኔ ነው” ብለዋል።
"አንራራልህም" ሲሉ
ክሃን ባለፈው ወር ባደረጉት ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ለአጋራቸው ዋስትና የከለከሉትን ዳኛ ስም በመጥቀስ እንምርህም የሚል ዛቻ አሰምተው ነበር ተብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ በፈረንጀቹ 22 በዋለው ችሎት የክሃን ክስ እንደሚያቀርብ ቻውድሪ ተናግሯል። ክሃን በንግግሩ ቢጸጸጹም በግልጽ ይቅርታ አልጠየቁም፡፡
ዳኞቹ የጉዳዩን ክብደት እንዳልተረዳው በመግለጽ የክሃንን ጠበቆች ሃሙስ ዕለት ደጋግመው ማስጠንቀቃቸውን ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡