የገዛ ሚስቱን በ50 ወንዶች ያስደፈረው ሰው በ20 ዓመት እስር ተቀጣ
ግለሰቡ ሚስቱ በማታውቅበት መንገድ በሚኖሩበት ቤት እንዳስደፈረ አምኗል
ለዓመታት ተፈጽሟል በተባለው ወንጀል ተከሳሹ ፍርዱ በዝቶብኛል በሚል ይግባኝ እንደሚጠይቅ ተገልጿል
የገዛ ሚስቱን በ50 ወንዶች ያስደፈረው ሰው በ20 ዓመት እስር ተቀጣ።
ዶምኒክ ፔሊኮት ፈረንሳዊ ሲሆን ለዓመታት የትዳር አጋሩን ሆን ብሎ ሲያስደፍር እንደነበር ተገልጿል።
በፓሪስ ከሚስቱ እና ሶስት ልጆቹ ጋር ይኖር ነበር የተባለው ይህ ግለሰብ ለዓመታት እንግዳ ሰዎችን ወደ መኖሪያ ቤቱ በማምጣት ሚስቱን እንዲደፍሩ አድርጓል ተብሏል።
ግለሰቡ ድርጊቱን የሚፈጽመው ሚስቱ ራሷን እንድትስት እና ህመሞችን እንድትቋቋም የሚያደርግ ማደንዘዣ መድሀኒት ያለ ፍቃዷ እንድትወስድ በማድረግ እንደነበር ኤኤፍፒ ዘግቧል።
ላለፉት 14 ዓመታት በተለያዩ ሰዎች ስትደፈር የነበረችው ሚስቱ ጉዳዩን ይዛ ወደ ፍርድ ቤት አምርታለች።
ጉዳዩ የሚዲያዎችን ትኩረት ካጉኘ በኋላ ፈረንሳይን ጨምሮ በመላው አውሮፓ አግራሞትን እና ቁጣን አስከትሏል።
ፖሊስ ግለሰቡን በሌላ ወንጀል ጠርጥሮት በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ በስልኩ ላይ ባደረገው ምርመራ አማካኝነት ሚስቱን ሲያስደፍር የሚያሳይ ምስል ይገኛል።
በማታውቀው መንገድ በባሏ አመቻችነት ስትደፈር እንደቆየች ከተረዳች በኋላ ክስ ምስርታ ስትከራከር ቆይታለች።
ይህች ሴት በባሏ አመቻቺነት በ50 ወንዶች 92 ጊዜ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባታል ተብሏል።
ወንጀሉን እንደፈጸመ የተናገረው ይህ ግለሰብ ይቅርታ እንዲደረግለት ጥያቄ እንዳቀረበ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
የ20 ዓመት እስር የተላለፈበበት ይህ ተከሳሽ ፍርዱ በዝቶብኛል በሚል ይግባኝ እንደሚጠይቅ ጠበቃው ለሚዲያዎች ተናግሯል።