የጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ የኢስዋትኒ ንጉስ 16ኛዋ ሚስት በመሆን ተሞሸረች
የጋብቻ ስነ ስርዓቱ ባሳለፍነው ሰኞ በኢስዋትኒ መዲና ሎባምባ ቤተ መንግስት ተካሂዷል
የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ብዙ ሚስቶች ያሏቸው ሲሆን 20 ልጆችንም አፍርተዋል
የጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ የኢስዋትኒ ንጉስ 16ኛዋ ሚስት በመሆን ተሞሸረች፡፡
ኖምችዶ ዙማ የ21 ዓመት እድሜ ያላት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ልጅም ናት፡፡
የደቡብ አፍሪካ ጎረቤት የሆነችው የቀድሞዋ ስዋዚላንድ የአሁኗ ኢስዋትኒ ንጉሳዊ ስርዓት ያላት ሀገር ናት፡፡
የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም በህግ የከለከለችው ይህች ሀገር በንጉስ ምስዋቲ ሶስተኛ በመመራት ላይ ትገኛለች፡፡
የ56 ዓመቱ የኢስዋትኒ ንጉስ የ21 ዓመቷን ኖምችዶ ዙማን 16ኛ ሚስት አድርገው ማግባታውን የሀገሪቱ ብዙሀን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ ጋብቻው 5 ሺህ ልጃገረዶች በተገኙበት ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቆ ተካሂዷል፡፡
ከሰሞኑ በምስራቅ አፍሪካ እየታየ የሚገኝው ውጥረት ምን ያህል አስጊ ነው?
ነጥብ 2 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢስዋትኒ ንጉስ ምስዋቲ አይናቸው ያረፈባትን ልጃገረድ የማግባት መብት የተሰጣቸው ሲሆን እስካሁን ያላቸው ሚስቶች 16 ደርሰዋል፡፡
አብዛኛው የሀገሪቱ ህዝብ በድህነት ውስጥ የሚኖር ነው የተባለ ሲሆን ንጉስ ምስዋቲ እጅግ ቅንጡ ህይወት እየኖሩ ነው በሚል ክስ ይቀርብባቸዋል፡፡
ሴት ልጃቸውን ለኢስዋትኒ ንጉስ የዳሩት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ከፈረንጆቹ 2009 እስከ 2018 ድረስ መርተዋል፡፡
ብዙ ሚስቶች ያሏቸው ዙማ 20 ልጆች ያሏቸው ሲሆን በአሁኑ የልጃቸው ባህላዊ ጋብቻ ላይ ይገኙ አይገኙ እስካሁን አልታወቀም፡፡