ፉሚዎ ኪሺዳ፤ ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሊመሩ ነው
በዚህም ዮሺሂዴ ሱጋን በቀናት ውስጥ ተክተው ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ይመራሉም ነው የተባለው
ኪሺዳ የመሪው የጃፓን ሊበራል ዲሞክራሲ ፓርቲ (LDP) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል
የቀድሞው የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉሚዎ ኪሺዳ የሃገሪቱ መሪ ፓርቲ፤ የጃፓን ሊበራል ዲሞክራሲ ፓርቲ (LDP) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡
የ64 ዓመቱ ፉሚዎ የፓርቲው አባላት ከሰጡት ድምጽ 257ቱን በማግኘትና የክትባት ሚኒስትሩን ታሮ ኮኖን በማሸነፍ ነው የፓርቲው ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት፡፡
ይህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋን በመተካት ቀጣዩ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የሚያስችላቸው ነው፡፡
የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ይቅርታ ጠየቁ
ከ5 ቀናት በኋላ በሚካሄድ ልዩ ስነ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሾማሉም ብለዋል የሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች፡፡
የሊበራል ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንትነታቸው በፈረንጆቹ እስከ መስከረም 30፣ 2024 ይዘልቃልም ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋን ከወር በፊት ስልጣን እንደሚለቁ አስታውቀው ነበር፡፡
ይህን ተከትሎም ነው ፓርቲው ተተኪውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመምረጥ የሚያስችለውን ምርጫ ያካሄደው፡፡
ፉሚዎ በኮሮና ቫይረስ የደቀቀውን የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት እንዲያገገም የማድረግ ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
ዮሺሂዴ ሱጋ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤን ተክተው ላለፈው አንድ ዓመት ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማገልገላቸው የሚታወስ ነው፡፡