ቻይና በግንቦት ወር ከሩሲያ ያስገባችው የነዳጅ መጠን ከፍተኛ ሆኖ ተመዘገበ
ሩሲያ ለቻይና ያቀረበችው የነዳጅ መጠን በግንቦት ወር ብቻ ወደ 55በመቶ ከፍ ብሏል
ቻይና ከሩሲያ ያስገባችው የነዳጅ መጠን ጭማሪ አንደኛ አቅራቢ የነበረችው ሳኡዲ አረቢያን ከደረጃዋ አፈናቅሏል
ቻይና በግንቦት ወር ከሩሲያ ያስገባችው ነዳጅ መጠን ቀደም ሲል በከፍተኛ መጠን ወደ ቻይና የምትልከውን ሳኡዲ አረቢያን አቅርቦት በልጧል።
ሩሲያ ለቻይና ዋና የነዳጅ አቅራቢ የነበረችውን ሳኡዲ አረቢያን በመብለጥ በግንቦት ወር ብቻ ያቀረበችው ወደ 55 በመቶ ከፍ ብሏል።
በምስራቅ ሳይቤሪያ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ቧንቧ መስመር የሚጓጓዙ አቅርቦቶችን እና ከሩሲያ እና ከሩቅ ምስራቅ ወደቦች የሚላኩ የባህር ላይ ጭነትን ጨምሮ የሩስያ ዘይት ወደ 8ነጥብ42 ሚሊዮን ቶን እንደሚደርስ የቻይና አጠቃላይ የጉምሩክ አስተዳደር መረጃ ያሳያል።
ይህ በቀን በግምት 1ነጥብ 98 ሚሊዮን በርሜሎች (ቢፒዲ) እና በሚያዝያ ወር ከ1ነጥብ 59 ሚሊዮን ቢፒዲ ሩብ ከፍ ያለ ነው።
ሩሲያ ምንም እንኳን በምእራባውያን ማእቀብ ስር ብትሆን የነዳጅ ዘይት ገዥ መፈላለግ መቻሏን ሮይተርስ ዘግቧል።
የቻይና አጠቃላይ የድፍድፍ ዘይት ፍላጎት በኮሮና እገዳዎች እና ኢኮኖሚው እየቀነሰ ሲሄድ ፣ ዋና አስመጪዎች ፣ ግዙፉን ሲኖፔክ እና ነጋዴ ዜንሁዋ ዘይትን ጨምሮ በቅናሽ ዋጋ የሩሲያን ዘይት መግዛታቸውን ጨምረዋል። ይህም ለቻይና ከምዕራብ አፍሪካ እና ከብራዚል የሚመጡ ተፎካካሪ አቅርቦቶችን ለመቀነስ ይረዳታል።
ሳዑዲ አረቢያ ሁለተኛዋ ትልቁን አቅራቢ ሆና ትከተላለች፣ በግንቦት 9 በመቶ በ7.82 ሚሊዮን ቶን ወይም 1.84 ሚሊዮን ቢፒዲ ለቻይና ገበያ አቅርባለች። ይህ ከኤፕሪል 2ነጥብ17 ሚሊዮን ቢፒዲ ቀንሷል።
ሰኞ እለት ይፋ የሆነው የቻይና የጉምሩክ መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ወር 260,000 ቶን የኢራን ድፍድፍ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባች ሲሆን ይህም ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ ለሶስተኛ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
አሜሪካ ኢራን ላይ ማዕቀብ ብትጥልም ቻይና የኢራን ዘይት መወሰዱን ቀጥላለች፣ አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች ሀገራት እንደ አቅርቦት ይተላለፍ ነበር። ቻይና ከኢራን የምታስገባው ከጠቅላላው ከምታስገባው 7በመቶ የሚሸፍን ነው ተብሏል።