የቡድን 20 መሪዎች የአቋም ሰነድ አጸደቁ
ሩሲያ ዩክሬን ላይ አድርጋዋለች የተባለን ወረራ የሚነቅፍና ሌሎችም ጉዳዮች የያዘው ሰነድ በቡድ 20 የመሪዎች ጉባኤ መጽደቁን ሮይተርስ ዘግቧል
16 ገጾች ያሉት ሰነዱ ምን አይነት ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንደጸደቀ እስካሁን የተባለ ነገር የለም
የቡድን 20 መሪዎች የአቋም ሰነድ ማጽደቃቸው ተገለጸ
በሮይተርስ እጁ የገባው የዓለም ዋነኛ የምጣኔ-ሀብት መሪዎች የቡድን 20 አገራት ረቂቅ መግለጫ አብዛኞቹ አባላት “ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት” አውግዘዋል ብሏል
ሰነዱ ጦርነቱ የዓለም ምጣኔ-ሀብት ድክመቶችን እያባባሰ ነው ብሏል።
በመሪዎቹ መግለጫ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት እጅግ አከራካሪ አንቀጽ ሆኖ የተገኘ ነው ሲሉ የአስተናጋጅ ሀገር ኢንዶኔዢያ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሁሉም ወገኖች ውጥረቱን እንዳያባብሱም አሳስበዋል።
ሮይተርስ በ20ዎቹ ታላላቅ የምጣኔ-ሀብት ባለቤት ሀገራት ጉባኤ ላይ መግለጫው መጽደቁን በርካታ የዲፕሎማሲ ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።
የቡድን 20 አባላት በዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ላይ ሊደርስ የሚችለው አደጋ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው የገለጹ ሲሆን፤ ማዕከላዊ ባንኮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለውን የዋጋ ንረት ለመግታት ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በረቂቁ ተረጋግጧል ነው የተባለው።
16 ገጾች ያሉት ረቂቅ ምን አይነት ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንደጸደቀ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።