ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሮም የገቡ ሲሆን የቻይናው ፕሬዘዳንት በጉባኤው ላይ በአካል እይገኙም
የቡድን 20 አገራት ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል።
የዓለማችንን ኢኮኖሚ ከአንድ እስከ 20 ደረጃ ድረስ በያዙ አገራት መካከል የሚካሄደው ይህ የቡድን 20 አገራት ጉባኤ ዛር በጣልያን ሮም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ኮሮና ቫየረስ ከተከሰተ በኋላ መሪዎች በአካል ተገናኝተው ይመክሩበታል የተባለው ይህ ጉባኤ ዛር ከሰዓት ይካሄዳል ተብሏል።
በዚህ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የዓለማችን ሁለተኛዋ ሀብታም አገር ቻይና ፕራዘዳንት ሺ ፒንግ ጉባኤውን በቪዲዮ እንደሚሳተፉ ሮይተርስ ዘግቧል።
የቡድን 20 አባል አገራት በሮም ጉባኤያቸው በከሮና ቫይረስ ክትባት ተደራሽነት ዙሪያ፤በአየር ንብረት ለውጥ እና በተቀዛቀዘው የዓለም ኦኮኖሚ ዙሪያ እንደሚወያዩ ዘገባው አክሏል።
የቡድን 20 አገራት ጉባኤ በፈረንጆቹ 1999 ዓመት በፋይናንስ ሚኒስትሮች እና ባንክ ገዢዎች የተመሰረተ ቢሆንም በ2008 ዓመት በአለም የኢኮኖሚ ቀውስ መፈጠሩን ተከትሎ የአገራት መሪዎች የሚመክሩበት ጉባኤ አድጓል።
ጉባአው የአውሮፓ ህብረት እና ከ1ኛ እስከ 19ኛ ድረስ ባሉ የአለማችን ሀብታም አገሮች የተመሰረተ ሲሆን እነዚህ አገራት የአለማችን 60 በመቶ ህዝብን ይወክላሉ።
80 በመቶ የአለማችን ሀብት በዚህ ጉባኤ አባል አገራት የተያዘ ሲሆን ላለፉት ሁለት አመታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሪዎቹ በአካል ተገናኘተው አያወቁም።
አሜሪካ፤ ቻይና፤ ሩሲያ፤ ህንድ፤ ጀርመን፤ ደቡብ ኮሪያ፤ ብራዚል፤ አውስትራሊያ፤እንግሊዝ፤ ጃፓን፤ጣልያን፤ ኢንዶኔዥያ፤ ቱርክ፤ሳውዲ አረቢያ፤ ካናዳ፤ ፈረንሳይ፤አርጀንቲና፤ ሜክሲኮ እና ደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 አባል አገራት ናቸው።