“G42” ቡድን በዓለም መንግስታት ጉባኤ ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶችን ይመራል ተባለ
“G42” ቡድን መቀመጫውን አረብ ኢምሬትስ ያደረገ የዓለማችን ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ቡድን ነው
የ2024 በዓለም መንግስታት ጉባኤ በአረብ ኢምሬትስ ዱባይ ይካሄዳል
መቀመጫውን አረብ ኢምሬትስ ያደረገው የዓለማችን ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ቡድን “G42” እና ተባባሪዎቹ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤ.አይ) ዙሪያ በዘርፉ ካሉ የአለም መሪዎች ጋር የሚያደርጉ ውይይቶችን እንደሚመራ ተገለጸ።
የአረብ ኤሚሬትስ የቴክኖሎጂ ቡድን “G42” በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፈር ቀዳጅ እና ቁልፍ አጋር በመሆን በዘንድሮው የዓለም መንግስት ጉባኤ እንደሚሳተፍም አስታውቋል።
“G42” ቡድን እና አጋሮቹ ስለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የወደፊት እጣ ፈንታ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ስላለው ከፍተኛ ተፅእኖ ከአለም ሀገራት መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርግም ተነግሯል።
በየዓመቱ የሚካሄደው የዓለም መንግስታት ጉባዔ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአረብ ኢምሬትስ ዱባይ እንደሚካሄድ ተመላቷል።
ጉባዔው መንግስታትን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እና የንግድ መሪዎችን የሚያሰባስብ ሲሆን፤ አለም አቀፍ ትብብርን ማስተዋወቅ እና መንግስታትን በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ እድገቶች መለወጥ የሚቻልበትን መንገድ ላይ ይመክራል።
“G42” ቡድን እና አጋሮቹ በዚህ ጉባዔ ላይ በልዩ ሁኔታ እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ሊሆን የቻለውም ቡድኑ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) አተገባበር እና ውሳኔ ሰጪነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው ሰፊ ልምድ ነው ተብሏል።
በዚህ ዓመት የዓለም መንግስት ጉባኤ "የወደፊቱን መንግስታት በመቅረጽ" በሚል ርዕስ ላይ የሚወያይ መሆኑም ታውቋል።
በጉባዔውም ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ የፖለቲካ መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የግሉ ሴክተር ድርጅቶች ወቅታዊ እና የወደፊት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚስችሉ አዳዲስ ዘዴዎች ላይ እንደሚመክሩም ተነግሯል።
በተጨማሪም “G42” ቡድን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በጤና አጠባበቅ እድገት እና የወደፊት የእንቅስቃሴ እይታ ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ይመራል።
በውይይቶቹ ላይ ከሚሳተፉት የG42 የስራ አስፈፃሚ አመራሮች መካከል…
-የጂ 42 ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፔፒንግ ዢያዎ፤ የአለምን ኢኮኖሚ ገጽታ በመቅረጽ ረገድ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያለውን ሚና ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ።
- ታላል አል-ካይሲ በጂ 42 የአለም ምርቶች እና ግንኙነቶች ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ፤ ሰዎችን ለማገልገል ኃላፊነት የሚሰማው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እንዴት ማዳበር እንደሚቻል ማብራሪያ ይሰጣሉ።
- ሀሰን ጃሲም አል ኖቫይስ፣ የM42 ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና የቡድን ስራ አስፈፃሚ፣ የጤና እንክብካቤን በቴክኖሎጂ እንዴት መቀየር እንሚቻል እና በጤና እንክብካቤ ውስጥ በስትራቴጂካዊ አጋርነት ፈጠራን ማጎልበት እንዴት እንደሚቻል ያወያያሉ።
- ሀሰን አል ሆሳኒ የ"ባያናት" ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ፤ የስፓሻል ኢንተለጀንስ በከተሞች እና ማህበረሰቦች ደህንነት ላይ ስለሚጫወተው ሚና ላይ የሚደረገው ውይይት ላይ ይሳተፋሉ።
- ዶ/ር አንድሪው ጃክሰን የኮር 42 ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ዋና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኦፊሰር፤ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አለም ውስጥ እየተስተዋሉ ስላሉ አዳዲስ ለውጦች እና ጫናዎች ዙሪያ ማብራሪየ ይሰጣሉ።
-ቶማስ ፕራሞትትሃም፣ የፕሪሳይት ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ በትልልቅ ዳታ ትንታኔ እና በሚቀጥለው ትውልድ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የመንግስትን ቅልጥፍና እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል ንግግር ያደርጋሉ።
- ሀሰን አል-ናቅቢ የአል ካዝነህ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ ከዳታ ማእከሎች ግንባታ፣ ዲዛይን እና አሠራር ጋር በተገናኘ የቅርብ ጊዜ እድገቶችን ይተነትናሉ።
“G42” ቡድን ቡድን ዋና ስራ አስፈጻ ፔፒንግ ዢያዎ በሰጡት መግለጫ፤ የዓለም መንግስታት ጉባዔ በዓመቱ የተመረጡ የዓለም ሀገራት መሪዎችን እና ታወቂ ግለሰቦችን በአንድነት በማሰባሰብ ዓለማቀፍ ትብብርን ማጠናከርና መሰረታዊ ለውጦችን መፍጠር ላይ ይመክራል ብለዋል።
“G42” ቡድን በሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ፈጠራ ውስጥ ግንባር ቀደም እንደመሆኑ ቡድኑ እና አጋሮወቹ በዘንድሮ የመንግስታት ጉባዔ ላይ የመሪነት ሚና መጫወቱ ጀኩራት እንደሚሰማውም ስራ አስፈጻው ገልጸዋል።