“G42” እና “NVIDIA” አየር ንብረት ቴክኖሎጂን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለማሳደግ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
“G42” መቀመጫውን አረብ ኢምሬትስ ያደረገ የዓለማችን ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ቡድን ነው
የቴክኖሎጂ ተቋማቱ ስምምነት በተለይም ትክከለኛ አየር ትንበያ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ነው
መቀመጫውን አረብ ኢምሬትስ ያደረገው የዓለማችን ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ቡድን “G42” የአየር ንበረት ቴክኖሎጂን ለማዘማን ከአሜሪካው NVIDIA/ኒቪዳ” ኩባንያ ጋር አጋርነት መመስረቱን አስታወቀ።
ሁለቱ ኩባንያዎች ስምምነት በዓለም ዙሪያ የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሻሻል በማሰብ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ.አይ) መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ላይ በማተኮር የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።
የ“G42” እና “NVIDIA/ኒቪዳ” ትብብር በ“NVIDIA Earth-2” ፕላትፎርም ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ሲሆን፤ ይህም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻ ኢንተለጀንስ) በመጠቀም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የአየር ንብረት ትንበያ ምስሎችን ለማቅረብ የሚያስችለ ነው።
ምዕራፍ 1
የ“G42” እና “NVIDIA/ኒቪዳ” ትብብር በመጀመሪያ ምዕራፍ የአየር ትንበያ ትክክለኛነትን ለማሳደግ የአየር ትንበያ በስኩዌር ኪሎ ሜትር መለየት የሚያስችል ሞዴል ማልማት ይሆናል።
በዚህም በአረብ ኢምሬትስ አቡዳቢ “የኦፕሬሽን እና ቴክኒካ ላብ” የሚቋቋም ሲሆን፤ ተቋሙም የጥናትና ምርምር ማዕከል በመሆን ሁለቱ ተቋማት በአየር ንብረት ላይ የሚሰሩት ስራ ዘላቂነት እንዲኖረው የሚያግዝ ነው ተብሏል።
ማዕከሉ ከ100 በላይ ፔታባይት የጂኦሎጂካል መረጃዎችን በመጠቀም ተስማሚ የአየር ንብረት እና የአየር ሁኔታ መፍትሄዎችን ለማዘጋጀት የሚደረጉ ጥረቶችን ለማሻሻልም ይረዳል።
የG42 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔንግ ዚያኦ "ከNVDIA ጋር የተደረሰው ስምምነት አርቴፊሸል ኢንተለጀንስን ለፈጠራ እና በተግባራዊ መፍትሄዎች ለመጠቀም ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል" ብለዋል።
"Earth-2” የአየር ንብረት ቤተ ሙከራ በአቡ ዳቢ መመስረት የሁለቱም ወገኖች አቅም እና እውቀት በመረጃ ትንተና አንድ ላይ በማምጣት ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ያስችላል ሲሉም ተነግረዋል።
ወሳኝ እርምጃ
የኒቪዲያ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ በበኩላቸው ከG42 ጋር ያለው ትብብር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም ትክከለኛነታቸው የተረጋገጠ የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳትና ለመተንበይ ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል።
የG42 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እውቀትን ከNVDIA የኮምፒዩተር ችሎታ ጋር በማጣመር በኢንዱስትሪዎች እና በስነ-ምህዳሮች ላይ ትርጉም ያለው ለውጥን የሚፈጥር የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ለማምጣት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።