ስፖርት
ዮሚፍ ቀጄልቻ በ3000 ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ክብረወሰን የሆነ ፈጣን ሰዓት አስመዘገበ
ዮሚፍ በውድድሩ ከዚህ ቀደም በሀይሌ ገ/ስላሴ ተይዞ የነበረን ክብረወሰን በ1.17 ሰከንድ ማሻሻል ችሏል
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ውድድሩን 7 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ ነው ያጠናቀቀው
በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል
ትናንት ምሽት በኖርዌይ፣ ኦስሎ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ክብረወሰን የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ነው ውድድሩን ያጠናቀቀው።
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 7 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ እንደፈጀበትም ነው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ መረጃ የሚያመላክተው።
ዮሚፍ ያስመዘገበው ሰዓት ቀደም ሲል በአትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በስፍራው ይዞ የነበረውን ክብረወሰን በ1.17 ሴኮንድ በማሻሳል መቻሉም ነው የተገለጸው።
በውድድሩ ሌላኛው የኢትዮጵያ አትሌት ታደሰ ወርቁ በ7:37.48 ሰዓት 7ኛ ወጥቶ ውድድሩን አጠናቅቋል።
በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ደግሞ ፋንቱ ወርቁ በ14:26.80 በመግባት 2ኛ ስትወጣ ፀሃይ ገመቹ በ14:38.76 ሰዓት በመግባት 6ኛ ሆና ውድድሩን ማጠናቀቋን ታውቀዋል።