ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከወዳጆቻቸው ጋር ለመነጋገር ጃፓን ሂሮሺማ ገቡ
የሂሮሺማ የቡድን ሰባት ጉባኤ አባላቱ በሩሲያና ቻይና ከፍተኛ ስጋት ውስጥ በገቡበት ወቅት የመጣ ነው
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከቡድን ሰባት ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሏል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከዓለማችን የበለጸጉ ሀገራት መሪዎች ለጦርነቱ ድጋፍ ለማሰባሰብ ጃፓን ሂሮሺማ ከተማ ገብተዋል።
በዓለም የኒውክሌር ጥቃትን ለመጀመሪያ ጊዜ በቀመሰችው ከተማ ዘለንስኪ በቡድን ሰባት ስብሰባ ላይ መገኘታቸው የምዕራባውያን መንግስታት በሩሲያ የተደቀነውን የኒውክሌር አደጋ ስጋት ላይ እንደሚያጤኑት ያደርጋል ተብሏል።
የሂሮሺማ ጉባኤ የቡድን ሰባት አባላት ሩሲያ በዩክሬን ላይ በጀመረችው ጦርነት እና ቻይና በታይዋን ላይ ባሳየችው አቋም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ በገቡበት ወቅት የመጣ ነው።
- የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ሜዳሊያ ሸለሙ
- የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ “የሩስያ አውዳሚ ጦርነት የሚያበቃበት ጊዜ አሁን ነው” አሉ
ዘለንስኪ በተለመደው ጎመኔ የወታደራዊ ልብሳቸው ከፈረንሳይ መንግስት አውሮፕላን ሲወርዱ ታይተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከዩክሬን አጋሮች እና ጓዶቻቸው ጋር አስፈላጊ ስብሰባ ሊቀመጡ መሆኑን በትዊተር ገጻቸው አጋርተዋል።
የፈረንሳይ እና የአውሮፓ ባለስልጣናት ዘለንስኪ በአካል መጀመሪያ ወደ አረብ ሊግ አሁን ደግሞ ቡድን ሰባት ማቅናታቸው "ወሳኝ" ነው ብለዋል።
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ባለስልጣን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "የዩክሬንን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅ አጋር ያልሆኑ መንግስታትን ለማስተሳሰር ሁሉንም መንገዶች መጠቀም አለብን" ብለዋል።
ዘለንስኪ ከቡድን ሰባት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ያካሂዳሉ መባሉንም ሮይተርስ ዘግቧል። የሞስኮ ወዳጅ ከሆኑት ከህንድ እና ብራዚል መሪዎች ጋርም ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።