ሩሲያ የፕሬዝደንት ዘለንስኪን “ወታደር የማስቀጣት ጥሪ” ውድቅ አደረገች
ሞስኮ ዩክሬን “የግዛት እውነታዎችን” መቀበል አለባት በማለት ጥሪውን አጣጥላለች
ዩክሬን እና ምዕራባውያን አጋሮቿ ሩሲያ ያካሄደችውን "ህዝበ ውሳኔ" በጠመንጃ አፈሙዝ የተካሄደ ነው ሲሉ ህገ-ወጥ በማለት አጣጥለውታል
ሞስኮ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ያቀረቡትን የሩሲያ ወታደሮች መውጣትን ያካተተ የሰላም ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች።
ሞስኮ ኪየቭ አዲስ የክልል "እውነታዎች" መቀበል አለባት በማለት ጥሪውን ውድቅ አድርጋለች።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንደተናገሩት እነዚህ እውነታዎች ሩሲያ አራት የዩክሬን ክልሎችን እንደ "ሀገሪቱ የግዛት አካል" ማካተቷን መቀበል አለባት። የተጠቃለሉት ግዛቶችን ባለፈው መስከረም ወር ያወጀችው ሩሲያ፤ አብዛኛዎቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት “ህገ-ወጥ” በማለት ተቃውመዋል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከፈረንጆቹ ገና ጀምሮ ሩሲያ ወታደሮቿን ከዩክሬን በማስወጣት የሰላም መፍትሄ ጥሪ ያቀረቡት ከቡድን ሰባት ሀገራት መሪዎች ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነበር።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ "ዩክሬን በዚህ ጊዜ ውስጥ [በጦርነቱ] የተፈጠረውን እውነታ ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት" ሲሉ የሩሲያ ወታደሮችን መውጣትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።
"እነዚህ እውነታዎች በሩሲያ ፌደሬሽን ውስጥ አዳዲስ ግዛቶች መከሰታቸውን ያመለክታሉ።
የተከሰቱትም በእነዚህ ግዛቶች ውስጥ በተደረጉ ህዝበ ውሳኔዎች ነው። እነዚህን አዳዲስ እውነታዎች ሳይቀበሉ ምንም አይነት ለውጥ ሊኖር አይችልም" ብለዋል።
ዩክሬን እና ምዕራባውያን አጋሮቿ ሩሲያ በከፊል በያዘቻቸው አራት የደቡብ እና ምስራቅ ዩክሬን ክልሎች ላይ የተካሄደውን "ህዝበ ውሳኔ" በጠመንጃ አፈሙዝ የተካሄደ ነው ሲሉ ህገ-ወጥ በማለት አጣጥለውታል።
ከግዛቶቹ ጥቅለላ በኋላ ሩሲያ በዩክሬን ደቡብ እና ምስራቃዊ አካባቢዎች ጉልህ ስፍራ ማጣቷን የጠቀሰው ሮይተርስ፤ ይህን ተከትሎም የሰላም ንግግሮችን ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗን ደጋግማ ተናግራለች ብሏል።
ነገር ግን ዩክሬንና የጦር መሳሪያ የሚያቀርቡት ምዕራባውያን ለድርድር ዝግጁ አይመስሉም ብላለች። ሞስኮ የዲፕሎማሲ ንግግር የምትጠይቀው የተሟጠጠ ኃይሏ ለ10 ወራት በሚጠጋ ጦርነት እንደገና ለማሰባሰብ ጊዜ በመፈለግ ነው የሚለውን ክስ ውድቅ አድርጋለች።