ፈዋሽ መድኃኒቶችን ለማወቅ ጉሬዛ እና ጦጣ የሚመገቧቸውን እጸዋት የሚያድኑት ተመራማሪዎች
ጉሬዛ ላይ በተደረገ ክትትል አራት ተክሎች ለተለያዩ ህመሞች ፈዋሽ ሆነው ተገኝተዋል
እንስሳቱ አዘውትረው ከሚመገቧቸው ተክሎች መካከል አራቱ መርዛማ ኬሚካሎችን ከማስወገድ ጀምሮ እስከ ጽንስ መጸነስ አለመቻል ላሉ ችግሮች መፍትሔ ሆነው ተገኝተዋል ተብሏል
ፈዋሽ መድኃኒቶችን ለማወቅ ጉሬዛ እና ጦጣ የሚመገቧቸውን እጸዋት የሚያድኑት ተመራማሪዎች
በእጸዋት ብዝሀ ህይወት ሀብት ከሚታወቁ ሀገራት መካከል አንዷ በሆነችው ጋቦን ለሰው ልጅ ህመሞች ፈዋሽ የሆኑ በሽታዎችን ለማከም እንደ ጉሬዛ ያሉ እንስሳትን እየተከታተለች ትገኛለች።
የጋቦን ተመራማሪዎች ከብሪታንያ አቻቸው ጋር በመሆን ጉሬዛ እና ጦጣ አይነት እንስሳት አዘውትረው የሚመገቧቸውን እጸዋት እየተከታተሉ በመመዝገብ ላይ ናቸው።
እንስሳቱ ፈልገው ይመገቧቸዋል የተባሉት እጸዋት በገጠራማው አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ህመም ሲሰማቸው የሚወስዷቸው እንደሆኑም ተገልጿል።
ቢቢሲ እንደዘገበው እስካሁን ጉሬዛ አፈላልጎ ሲመገባቸው ከታዩ እጸዋት ውስጥ አራቱ በተመራማሪዎቹ ተለይተዋል።
ተመራማሪዎቹ እጸዋቱ ላይ ባደረጉት ምርምር በሰው ልጆች የሰውነት አካል ውስጥ ያሉ መርዛማ ኬሚካሎችን ለማስወገድ የሚጠቅሙ ሆነው ተገኝተዋል።
ይሄው ጉሬዛ የተሰኘው የዱር እንስሳ አዘውትሮ ከሚመገበው እጽ ውስጥም አንዱ በመድሀኒት መላመድ ምክንያት የሚጎለብቱ ባክቴሪያዎችን የማጥፋት አቅም እንዳለውም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።
የአካባቢው ማህበረሰቦችን ባካተተ መልኩ እየተካሄደ ያለው ይህ መድሀኒቶችን ከእጸዋት ውስጥ የመፈለግ ሂደት የሆድ ውስጥ በሽታዎችን ጨምሮ እስከ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ሰዎች መፍትሔ ይሆናሉም ተብሏል።